የህወሓት መግለጫ እና አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 11.07.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የህወሓት መግለጫ እና አስተያየት

ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ማክሰኞ ሐምሌ 2 2011 ካደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ በርካታ ጉዳዮች የዳሰሰ መግለጫ አውጥቷል። የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ የተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ዳሷል። መግለጫው ከተለያዩ አካላት ድጋፍና ተቃውሞ እያስተናገደ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:29

የሕወሐት ማስጠንቀቂያ

ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ማክሰኞ ሐምሌ 2 2011 ካደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ ያወጣዉ መግለጫ በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ዳሷል። በቅርቡ በከፍተኛ የሠራዊት አመራሮች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተም ጉዳዩን በሀገራዊ ገለልተኛ ወገን እንዲጣራ የጠየቀ ሲሆን ውጤቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።  የሀገሪቱ ህልውና "ከመጥፎ ወደ ከፋ ደረጃ ተሸጋግሯል" ያለው ህወሀት የችግሮቹ ዋነኛ ምንጭም "የህዝብን መብትና ጥቅም ረግጠው ፍላጎታቸውን ሊፈፅሙ የሚፈልጉ የትምክህት ሀይሎች" ናቸው ብሏል።  መግለጫው ከተለያዩ አካላት ድጋፍና ተቃውሞ እያስተናገደ ነው።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic