የህክምና ተማሪነት በጀርመን | ባህል | DW | 05.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የህክምና ተማሪነት በጀርመን

የዛሬው የወጣቶች አለም ፤ በጀርመን ሀገር የህክምና ትምህርት የምታጠና እና በአሁን ሰዓት ለስራ ልምምድ በኢትዮጵያ የምትገኝ ወጣትን ያስተዋውቃል።

እስቲ ስንቶቻችን ነን ፤ ትልቅ ስትሆኚ ወይንም ስትሆን ምን መሆን ትፈልጋላችሁ ስንባል፤ ዶክተር፣ ፓይለት ወይንም ሳይንቲስት ያልን። በርግጥ በልጅነት ያልነው እና አሁን ለመማር የምንፈልገው ወይንም የተማርነው ያኔ ያልነው ነውን? የዛሬው እንግዳችን- ሰብለወንጌል የመኔ -የልጅነት ምኞቷን እየተማረች ነው። የህክምና ትምህርትን።

BU: Hightech im OP-Saal Bildbeschreibung: OP-Saal mit Technik wie im Cockpit, verschiedene Monitore und OP-Tisch in der Mitte (Seitenaufnahme) Photo: IRDC Leipzig

በጀርመን- ላይብዚግ ከተማ አንድ የቀዶ ህክምና ክፍል

የህክምና ትምህርት ቢያንስ ስድስት ዓመት ተኩል ይፈጃል። በዚህ ረዥም የትምህርት ጊዜዋ ሰብለወንጌል የገጠሟትን ፈተናዎች አጫውታናለች።

ከጀርመን ሀገር ወደ ጎንደር ሄዳ በአሁኑ ሰዓት የስራ ልምምድ በማድረግ ላይ ያለችው የህክምና የመጨረሻ አመት ተማሪ -ሰብለወንጌል በጎንደር በተወሰኑ እና ዘመናዊ ባልሆኑ መሳሪያዎች መስራትን እንዴት ለመደችው? በምኞት ደረጃ የህክምና ትምህርትን ለመከታተል ለሚጥሩ ወይንም በመማር ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንስ ሰብለወንጌል ምን ታካፍላለች? ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic