የሄልሙት ሽሚድት ሕልፈትና የሐዘን መግለጫዎች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 11.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሄልሙት ሽሚድት ሕልፈትና የሐዘን መግለጫዎች

የቀድሞዉ የጀርመን መራሔ መንግሥት ሄልሙት ሽሚድት ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ተከትሎ በርካታ የዓለም መንግሥታትና የመንግሥታት ተጠሪዎች ለጀርመን የኃዘን መግለጫዎቻቸዉን እያስተላለፉ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:37

ሄልሙት ሽሚድት ዜና ረፍትና የፖለቲከኞች የሃዘን መግለጫ


የጀርመን በተለይ የሃንቡርግ ከተማ ነዋሪዎች የ 96 ዓመቱ ሄልሙት ሽሚድት መኖርያ ቤት አጠገብ በመሄድ ሻማ በማብራትና አበባ በማስቀመጥ ኃዘናቸዉን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ። በጀርመን ሕዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩት ሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ አባልና የፖለቲካ ጉዳይ ተንታኝ ሄልሙት ሽሚዲት ባደረባቸዉ ሕመም ምክንያት፤ በመኖርያ ቤታቸዉ በሕክምና ሲረዱ ቆይተዉ ነዉ ትናንት ከቀትር በኋላ ሕይወታቸዉ ማለፉ የተነገረዉ ። የጀርመን ፖለቲከኞች የሄልሙት ሽሚትድን ከዚህ ዓለም በሞት መለየት በተመለከተ የሰጡትን አስተያየቶች የተካተካተበትን ዘገባ የበርሊኑ ወኪላችን አሰናድቶ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

አeያም ተክሌ

Audios and videos on the topic