የሃጅ ዝግጅት በእስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት | ኢትዮጵያ | DW | 06.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሃጅ ዝግጅት በእስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት

አቅሙ ያለዉ የእስልምና ሃይማኖት ተከተይ በእድሜዉ አንድ ግዜ ሳዉዲ ወደሚገኘዉ መካ መሄድ ወይም ሃጅ ማድረግ ግዴታ መሆኑን የሃይማኖቱ አባቶች ይናገራሉ። ብዙዎች ሃጅ የሚደርጉትም በእዲ አል አዳሃ ወይም በአረፋ በዓል ወቅት ነው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:24

የሃጅ ዝግጅት

አረፋ በሚቀጥለው ዓመት እሁድ ምስከረም 1, 2009 ዓም ነው የሚውለው ። በዚህ ወቅት ላይ ከኢትዮጵያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ወደ ሜካ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።


በዚህ ዓመት በቀን 368 ሃጃጆች ወደ መካ ይሄዱ እንደነበር ያስታወቀው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ በቀን 1000 ሃጃጆችን ለማጓጓዝ ቅድም ዝግጅቶችን መጨረሱን ተናግሯል።

ለዚሁ ጉዞም ከነገ ወዲያ ረቡዕ, ሴኔ 1, 2008 ዓም ምዝገባ ለመጀመር እንደተዘጋጀ የምክር ቤቱ ስራ አስፈፃም እና የሃጅና ዑምራ ዘርፍ ሃላፊ ሼክ አህሜድ ዙሱፍ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በህጅራ አቆጣጠር «ዱሁል ቃዳህ 22፣ 1437 ማለትም እንደጎርጎረሳዊያን አቆጣጠር ሐሙስ፣ ነሐሴ 19፣ 2008 ጉዞ ወደ መካ የሚጀመርበት ዕለት ነው ። በዚህ ዓመት ቪዛ ማግኘት እና ሌሎች ለጉዞ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ለመጨረስ አስቸጋሪ እንደነበር ከተጓዦቹ ቅሬታዎች ሲሰሙ ነበር። በተጨማሪም ውስን የነበረው እና የተወጣጠረው የበረራ አገልግሎት ብዙዎችን አስኮርፈዋል። ሼክ አህሜድ ለሚቀጥለው ጉዞ ካለፈዉ ችግር ተምረናል ይላሉ።

ባለፈዉ ዓመት በመካ በግፍያ ምክንያት በተከሰተዉ አደጋ ከ1453 በላይ ሰዎች ሞተዋል ። በምክርቤቱ በኩል ለተጓዞች ስለ ደህንነት ጥበቃ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ አለ ወይ ብለን ጠይቀን ነበር፣

በሃጂ 9ኛዉ ቀን ላይ ዱአ በሚደረግበት አረፋ ተብሎ በሚጠራ ተራራ ለኢትዮጵያ በተሰጠው ቦታ ተጓዦች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ሼክ አህመድ አሳስበዋል።

መርጋ ዮናስ
ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic