የሃይማኖት ግጭቶች የምክክር መድረክ | ኢትዮጵያ | DW | 04.07.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሃይማኖት ግጭቶች የምክክር መድረክ

በኢትዮጵያ የሚከሰቱ የሃይማኖት ግጭቶች መንስኤ የሃይማኖቶችን ተልዕኮ እና ዓላማ አለማወቅ መሆኑን አንድ የዓለም የዕርቅና የሰላም ግብረ ሠናይ ድርጅት የሥራ ሃላፊ አስታወቁ ።

default

የዓለም የዕርቅና የሰላም ግብረ ሠናይ ድርጅት የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ሊቀ መንበር ዶክተር ያዕቆብ በቀለ በቅርቡ ስለ ደረሱ የሃይማኖት ግጭቶች መንስኤ ከዶቼቬለ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ቃለ ምልልስ የችግሩ መነሻ ህብረተሰቡ ስለ ሃይማኖቱ የጠለቀ እውቀት አለመጨበጡ መሆኑን ተናግረዋል ። በኢትዮጵያ በተለያዩ ጉዳዮች ሰበብ የሚነሱ ግጭቶችን በእርቅና በሽምግልና ለመፍታት የሚንቀሳቀሰው የዓለም የሠላምና የእርቅ ግብረ ሰናይ ድርጅት ባላፈው አርብ አዲስ አበባ ውስጥ በኢትዮጵያ በየጊዜው የሚነሱ የሃይማኖት ግጭቶችን በተመለከተ የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ ነበር ።

ታደሰ እንግዳው


ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic