የሃይማኖት አባቱ የጀርመን ተሞክሮ | ባህል | DW | 06.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የሃይማኖት አባቱ የጀርመን ተሞክሮ

«እንዳገለግል የተመደብኩበት ቦታ በርሊን ከተማ ነዉ፤ በርሊን ደግሞ ለሃይማኖት ብዙም ቦታ የማይሰጥበት ነዉ፤ ይህ ሁኔታ ለኔ እንግዳ ነገር ነበር፤ እንደዛም ቢሆን ግን ለሃይማኖተኞች የማይመች ከተማ ነዉ ማለት ግን አይቻልም።» የበርሊን ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ-ክርስትያን አስተዳዳሪ የነበሩት መልዓከ ገነት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 16:22

የአባ ብርሃነ መስቀል የጀርመን ተሞክሮ፤

የበርሊን ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ-ክርስትያን አስተዳዳሪ የነበሩት መልዓከ ገነት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ ፤ በቅርቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደዉ ስብሰባ  ለኢጲስ ቆጶስነት ከተመረጡት 16 ቆሞሳትአንዱ ናቸዉ።  ለ16 ዓመታት በዉጭ በሚገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ያገለገሉት መልዓከ ገነት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ 14ቱን ዓመት ያሳለፉት በበርሊን የሚገኘዉን የደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ-ክርስትያንን በማስተዳደር ነዉ። 

 የበርሊን ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ-ክርስትያን አስተዳዳሪ የነበሩት መላከ ገነት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ።

የበርሊን ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ-ክርስትያን አስተዳዳሪ የነበሩት መላከ ገነት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ።

በግንቦት ወር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደዉ ስብሰባ ላይ ለኢጲስ ቆጶሳትነት ከተመረጡት 16 ቆሞሳት መካከል በጀርመን የነበሩ ሁለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን አባቶች ለኢጲስ ቆጶሳትነት ተመርጠዉ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል። በሙኒክ/ደ/ብ/ቅ ገብርኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ የሆኑት ሊ/ብ ቆሞስ አባ ገ/ሕይወት ፍሥሓ እና የበርሊን ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ-ክርስትያን አስተዳዳሪ የነበሩት መላከ ገነት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ ናቸዉ። ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ ሳምንታትን ያስቆጠሩትና በበርሊን ከ 14 ዓመታት በላይ የኖሩት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላን ያገኘናቸዉ ወደ ኢትዮጵያ ስልክ በመደወል ነበር።  ወቅቱ አሁን በጀርመን በጋ ሞቃታማ ነዉ። ኢትዮጵያ ደግሞ ክረምት ነዉ ዝናቡም ብርዱም ጠንከር ያለ ነዉ ሲሉ ነበር አባ ብርሃነ መስቀል ቃለ- ምልሳቸዉን የጀመሩት፤ የዛሬ 16 ዓመት ወደ ጀርመን ሲመጡ ክረምት ወራት እንደነበር ባዘቶ ጥጥ የመሰለ ብን ብን የሚል በረዶ ይጥል እንደነበርም አባ ብርሃነ መስቀል ያስታዉሳሉ።    

አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ፤ በርሊን እንኳን ደህና መጣህ ሲል የመልካም ምኞት የገለፀልኝ ሲሉ እንደ አበባ የመሰሉት ብን ብን የሚለዉ የክረምት በረዶ አይነት አስገርሟቸዋል። የመጡበትን የሃይማኖት አገልግሎትን በጀርመን ሃገር እንዴት አግኝተዉት ይሆን?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነትን የተቀበሉ ጀርመናዉያን ቁጥር ቤተክርስትያኒትዋ በጀርመን ከተመሰረተችበት ዓመት ጋር ሲነፃጸር ጥቂት እንደሆነ የተናገሩት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ፤ እንድያም ሆኖ የድቁና ትምህርትን አጠናቆ ግዕዝንም ተምሮ ቤተክርስትያኒትዋን በማገልገል ላይ የሚገኝ ጀርመናዊ እንዳለ ተናግረዋል። 

በቅርቡ በበርሊንና አካባቢ የሚኖረዉ ምዕመን ገንዘብ አዋቶ ቤተ ክርስትያን ገዝቶአል እና ይህ ዉድ አይሆንም ? ከባድ አልነበረም?  

በርሊን የምትገኘዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን፤ የዓለም አብያተ ክርስትያናት ምክር ቤት አባል መሆንዋን የገለፁት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ፤ ጀርመን ዉስጥ  የተለያዩ እምነቶች በጋራ ስብሰባ ዉይይት ሲያካሂዱ ቤተክርስትያኒቱ እንደምትካፈል ገልፀዋል።

እንግዲህ ብዙ ምዕመናን ብዙ የእርሶ ቤተሰቦች ብዙ የእርሶ ልጆች በመሄድዎ አዝነዋል በርግጥ ወደ አገር ቤት ወደ ኢትዮጵያ መሄድዎ ያስደስታል፤ቢሆንም ብዙዎች አዝነዋል።

መላከ ገነት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ ከጀርመን ምን ይዘዉ ሄደዉ ይሆን? ከጀርመናዉያን ይሄን ተምሬ ይሄንን ይዤ ተመልሻለሁ የሚሉት ነገርስ ይኖራቸዉ ይሆን?፤      

ቃለ- ምልልስ የሰጡንን መላከ ገነት አባ ብርሃነ መስቀል ተድላን በዶይቼ ቬለ ስም በማመስገን ሙሉዉን ቅንብር እንዲያደምጡ እንጋብዛለን።

 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic