የሃበሻ የንግድ ማስተዋወቂያ በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሃበሻ የንግድ ማስተዋወቂያ በጀርመን

ኢትዮጵያንና ኤርትራውያን በብዛት የሚገኙት በታላላቆቹ የጀርመን ከተሞች ነው ። በተለያዩ ከተሞች መፅሄቱን በማከፋፈል ላይ የሚገኘው እዮብ እንደሚለው የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ቁጥር ከፍተኛ በሆነባቸው ከተሞች የንግድ እንቅስቃሴያቸውም የዚያኑ ያህል ያደገ ነው ።

ጀርመን ውስጥ በተለያየ የግል ሥራና በንግድ  የተሰማሩ  ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አገልግሎቶቻቸውንና ንግዶቻቸውን ሊያስተዋውቁ የሚችሉበት  መፅሄት በቅርቡ ታትሞ  በመሰራጨት ላይ ነው  ።  ጀርመን ውስጥ  ለተጠቃሚዎች ሲቀርብ ቢያንስ ከቅርብ አመታት ወዲህ የመጀመሪያው ሊባል የሚችለው ይኽው መፅሄት  የዛሬው አውሮፓ ና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ። ጥሩ እቃ ወይም ጥሩ ሥራ ፣ ማስታወቂያ አያስፈልገውም ይባላል ። ሆኖም  አንድ ንግድ ፣ አገልግሎት ወይም ምርት ጥሩም ቢሆን ቢያንስ እንዴትና የት ሊገኝ እንደሚችል ካልታወቀ ለተጠቃሚው  የሚደርስበት መንገድ ውሱን መሆኑ አያጠያይቅም ። ጥቅሙ ለአግልግሎት አቅራቢው ብቻ ሳይሆን ለተጠቃሚውም የሆነው ማስታወቂያ ባለንበት ዘመን በልዩ ልዩ  መንገዶች ይሰራጫል ።

Fasika äthiopisches Restaurant in Köln

የኮሎኙ ፋሲካ ምግብ ቤት

ከነዚህም አንዱ Yellow pages የሚባለው የንግድና የአገልግሎቶች ማስተዋወቂያ  ነው ። በየንግዱ ዘርፍ ተከፋፍሎ በሚቀርበው በዚህ መፅሄት ነጋዴዎችና በልዩ ልዩ የሥራ መስከች የተሰማሩ ባለሞያዎች አገልግሎታቸውንና ምርቶቻቸውን ያለ ውጣ ውረድ በቀላሉ ያስተዋውቁበታል ። በውጭው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ንግዳቸውንና ሙያቸውን ከሚያስተዋውቁባቸው መንገዶች ውስጥ Yellow pages አንዱ ነው ።  መጀመሪያ ታትሞ በቀረበበት ወረቅት በቢጫ ቀለም የተሰየመው ይህ የማስታወቂያ መንገድ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በብዛት በሚኖሩባቸው በአንዳንድ የአውሮፓ ሃገራትና በሰሜን አሜሪካ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ቢሆንም በጀርመን ግን መሞከሩ እንጂ መዝለቁ አልተሰማም ። በጀርመን በስፋት የ4ተኝነቱን ደረጃ ከያዘችው ትልቅ ከተማ ኮሎኝ 13 ኪሎ ሜትር

ፈንጠር ብላ በምትገኘው Bayer የተባለው ታዋቂው የመድሐኒት ፋብሪካ በሚገኝባት ሊቨርኩዘን በተባለችው መለስተኛ ከተማ የሚኖረው  አቶ እዮብ አሰገዶም በቅርቡ የሃበሻ የንግድና የሙያ ማስተዋወቂያ መፀሀፍ ሲል የሰየመውን አዲስ Yellow pages አሳትሟል  ።

የተለያዩ  የአገልግሎት ሰጭዎችን  አድራሻዎች  ያካተተው የመጀመሪያው የሃበሻ የንግድና የሙያ ማስተዋወቂያ መፅሄት5 ሺህ ቅጂዎች  በመሰራጨት ላይ ናቸው ።   ከ 15 አመታት በላይ ጀርመን የኖረው እዮብ እንደሚለው ሥራውን የጀመረው በድፍረት ነው  ። ግን ያሰበው ሁሉ በአጭር ጊዜ ይሳካል ብሎም አልተነሳም ።

በማስታወቂያ ሥራ ውስጥ የአዘጋጁ ዋነኛ ተግባር ደንበኛ ለማግኘት ማግባባትና ማሳመን ነው የሚሆነው ። ደንበኛን ለመሳብም ልዩ ልዩ ዘዴዎችን መጠቀምም ያሻል ። መጀመሪያ መጎዳት ሊኖር እንደሚችል ገምቶ መፅሄቱን ማሳተሙን የሚናገረው እዮብ ያዋጣኛል ባለው መንገድ  ስራውን እያካሄደ ነው  ።   

Eine Deutsche braut in Frankfurt äthiopischen Honigwein - und ist damit über die Grenzen des Landes hinaus bekannt Copyright: Azeb Tadesse Hahn / DW

ኢትዮጵያንና ኤርትራውያን በብዛት የሚገኙት በታላላቆቹ የጀርመን ከተሞች ነው ። በተለያዩ ከተሞች መፅሄቱን በማከፋፈል ላይ የሚገኘው እዮብ እንደሚለው የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ቁጥር ከፍተኛ በሆነባቸው ከተሞች የንግድ እንቅስቃሴያቸውም የዚያኑ ያህል ያደገ ነው ።  

በአማርኛ  በትግርኛና በጀርመንኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀው የሃበሻ የንግድና የሙያ ማስተዋወቂያ መፅሄት በመጀመሪያው እትሙ ያስተወወቀው በርሊን ፍራንክፈርት ኮሎኝ ሙንሽን ኑርንበርግና ሽቱትጋርት ከተሞች የሚገኙ ምግብ ቤቶችንና ሱቆችን እንዲሁም የተለያየ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን ነው ።  በ2 ተኛው እትሙ  ደግሞ የሌሎች ከተሞችን  የንግድ እንቅስቃሴዎችን የማካተት እቅድ  አለው ።

ባለትዳርና የ 2 ልጆች አባት እዮብ የመፅሄቱ  ሥራ ከከተማ ከተማ የሚያዘዋውረው በመሆኑ ለቤተሰቡ መስጠት ያለበትን ጊዜ ይሻማበታል ። ሆኖም በባለቤቱ ድጋፍ ሥራውን መቀጠል መቻሉን ይናገራል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic