የሁለት ድርጅቶች ፍቃድ ተሰረዘ፤ የሁለቱ ደግሞ ገንዘባቸው ታገደ | ኢትዮጵያ | DW | 08.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሁለት ድርጅቶች ፍቃድ ተሰረዘ፤ የሁለቱ ደግሞ ገንዘባቸው ታገደ

የኢትዮዽያ የበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ እርምጃ የወሰደባቸው አራት ድርጅቶች ናቸው። ሁለቱ ሀገር በቀል፤ ሁለቱ ደግሞ የውጭ ድርጅቶች ናቸው።

default

የሀገር በቀሎቹ ገንዘባቸው ሲታገድ የውጭዎቹ ፍቃዳቸው ተነጥቋል። አቶ አህመድ ሰይድ በበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ የኮሚኒኬሽን ከፍተኛ ኤክስፐርት ኤጀንሲው የወሰደውን እርምጃ ገልጸዋል። የውጭዎቹ ሁለቱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህገወጥ ስራ ሲያከናውኑ የተገኙ በመሆናቸው ፍቃዳቸው ሊነጠቅ እንደቻለ ይናገራሉ። ሀገር በቀል የሆኑትና የገንዘብ እገዳ የተጣለባቸው ሁለቱ ድርጅቶች የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ(ሰመጉ) እና የኢትዮዽያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ናቸው። ሰመጉ በባንክ ያለው ገንዘብ ለ18 ዓመታት ያጠራቀምኩት እንጂ ከማንኛውም ወገን የተሰጠኝ አይደለም ሲል የመንግስትን መግለጪያ ያስተባብላል።

መሳይ መኮንን

አርያም ተክሌ

ተዛማጅ ዘገባዎች