የሁለቱ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የነገ ህልም | ባህል | DW | 20.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የሁለቱ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የነገ ህልም

ወቅቱ የአለም የእግር ኳስ ዋንጫ የሚተላለፍበት፣ ከልጅ እስከ አዋቂው ወንድ ሴት ሳይል ከቴሌቪዥን ፊት ለፊት ተቀምጦ ከብራዚል የሚተላለፉትን የእግር ኳስ ግጥሚያዎች የሚመለከትበት ነው።

የዛሬዎቹ የወጣቶች ዝግጅት እንግዶቻችን የእግር ኳስ ጨዋታውን የሚመለከቱት ከአብዛኞቻችን ለየት ባለ መልኩ ነው። ፍረ እግዚ መንግሥቱ እና ጋቶች ፋኖም ይባላሉ። አንዱ አቅዶ ሌላኛው እንደቀልድ ነው የእግር ኳስ ተጫዋች የሆኑት። ዛሬ ሁለቱም የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ተጫዋቾች ናቸው።

የ21 ዓመቱ ፍረ እግዚ የሞጆ ልጅ ነው። ወደ አዲስ አበባ ከመሄዱ በፊት ድሬ ድዋ ላይ በተካሄደ ውድድር ተካፍሎ በመጀመሪያ «ተስፋ» የሚባል ቡድን ገባ ።ከዛም ስድስት ወር ባልሞላ ጎዜ ባሳየው ጥሩ ውጤት የተነሳ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን እንደተቀላቀለ ይናገራል። በ 2003 ዓ ም ማለት ነው።

ከፍረ እግዚ ጋር አብሮ የሚጫወተው የ23 ዓመቱ ጋቶች ደግሞ ጋምቤላ ውስጥ ነው ተወልዶ ያደገው። ኳስ መጫወት የጀመረው የግድ ኳስ ተጫዋች እሆናለሁ በሚል አልነበረም። በኋላ ግን በክልል ባደረገው ውድድር ወደ አዲስ አበባ ሄዶ ለቡና ክለብ ለመጫወት እድል አገኘ።

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ፍረ እግዚ መንግሥቱ እና ጋቶች ፋኖም ሌላም ስለ ራሳቸው እና በብራዚል ስለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ያሉን አለ። ከድምፅ ዘገባው ተከታተሉት።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic