የሁለቱ ሱዳኖች ሥምምነትና ገቢራዊነቱ | አፍሪቃ | DW | 04.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሁለቱ ሱዳኖች ሥምምነትና ገቢራዊነቱ

አሁን በተቃራኒዉ ፔልስ እንደሚለዉ፥ ሁለቱም ሐራራ ያናወዘዉ ሰዉ ምሱን እሲኪያገኝ እንደሚቅበዘበዘዉ የነዳጅ ምርቱ እሲከጀመር እየተጣደፉ ነዉ።በሱዳን የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልክተኛ አንድሪዉ ናትሲዮስ እንደሚሉት ሱዳኖች የነዳጅ ምርቱን ለመጀመር ቢጣደፉ አይበዛባቸዉም።ሁለቱም የዚያ «ጥቁር ፈሳሽ» ጥገኛ ናቸዉ።

KHARTOUM, SUDAN: Leader of the Sudan People's Liberation Movement (SPLM), Salva Kiir (L), holds hands with Sudanese President Omar al-Bashir (C) and second Vice President Ali Osman Taha at a low-key ceremony in Khartoum 11 August 2005, during which Kiir was sworn in as Sudan's first vice president after the death of his predecessor John Garang. Kiir, 54, pledged to follow his legacy and work for peace and unity in the war-ravaged country. He took office less than two weeks after Garang was killed in a helicopter crash that raised fears for the future of a peace deal that ended 21 years of war between southern rebels and the government in Khartoum. EDS NOTE: Removing extraneous sentence. AFP PHOTO/KHALED DESOUKI (Photo credit should read KHALED DESOUKI/AFP/Getty Images)

እንደገና ወዳጅነት

04 04 13የሠሜንና የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት ባለፈዉ ወር ማብቂያ በተፈራረሙት ዉል መሠረት በአዋሳኝ ድንበሮቻቸዉ ላይ የሠፈሩ ወታደሮቻቸዉን ዛሬ ማንሳት ይጀምራሉ።ሁለቱ መንግሥታት ካለፈዉ ዓመት ጥር ጀምሮ ደቡብ ሱዳን አቋርጣዉ የነበረዉን የነዳጅ ዘይት ምርትና ሽያጭ ለመጀመርም ተስማምተዋል።ከሥምምነቱ በሕዋላ እንዳዲስ የተጀመረዉን ግንኘነት ለማጠናከር የሠሜን ሱዳኑ ፕሬዝዳት ዑመር ሐሰን አል-በሽር ጁባን እንዲጎበኙ የደቡቡ አቻቸዉ ሳልቫ ኪር ያቀረቡላቸዉን ግብዣ ተቀብለዋል።የዶቸ ቬለዉ ዳንኤል ፔልስ እንዘገበዉ የሁለቱ ሱዳኖች አዲስ ወዳጅነት ነዳጅ ዘይት ከሚያፈራዉ የጋራ ጥቅም ባለፍ ዳር መዝልቁ ግን አጠያያቂ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ ዝር ዝሩን አጠናቅሮታል።

እንዲያዉ በደፈናዉ ከደቡብ ሱዳን ነፃነት በኋላ ሁለቱን የሚያተከትከዉ ነዳጅ ነዉ።የሚያሰክነዉም ነዳጅ።ደቡብ ሱዳን ባለፈዉ ዓመት ጥር የነዳጅ ምርቷን ለማቋረጥ በርግጥ ሰበብ ነበራት።ሰሜን ሱዳንን በግዛቷ ከተዘረጋዉ የነዳጅ ቧምቧ፥ ነዳጅ ሰረቀቺኝ የሚል ዉንጀላ-አለበት።ሰበቡ ምክንያት መሆኑ ሳይረጋገጥ ግን የነዳጅ ምርቱን ለማቋረጥ መጣደፏ-እንጂ ግራዉ።

A Sudanese soldier poses with a machine gun in the oil town of Heglig bordering with South Sudan on April 24, 2012. South Sudan's leader accused Sudan of declaring war as Khartoum's warplanes bombed border regions in defiance of international calls for restraint. AFP PHOTO/EBRAHIM HAMID (Photo credit should read EBRAHIM HAMID/AFP/Getty Images)

የአዋሳኙ ድንበር ገሚስ ገፅታአሁን በተቃራኒዉ ፔልስ እንደሚለዉ፥ ሁለቱም ሐራራ ያናወዘዉ ሰዉ ምሱን እሲኪያገኝ  እንደሚቅበዘበዘዉ የነዳጅ ምርቱ እሲከጀመር እየተጣደፉ ነዉ።በሱዳን የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልክተኛ አንድሪዉ ናትሲዮስ እንደሚሉት ሱዳኖች የነዳጅ ምርቱን ለመጀመር ቢጣደፉ አይበዛባቸዉም።ሁለቱም የዚያ «ጥቁር ፈሳሽ» ጥገኛ ናቸዉ።
      
«የነዳጅ ፍሰቱ ሲቆም የሁለቱንም ምጣኔ ሐብት ክፉኛ ነዉ የጎዳዉ።ሁሉቱ ቢጠላሉምና የረጅም ጊዜ የግጭት ታሪክ ቢኖራቸዉም፥ በምጣኔ ሐብቱ መስክ ካልተባበሩ ሁለቱም መንግሥታት፥ ሁለቱም ማሕበረሰቦች በጣም አሳሳቢ ድቀት ይገጥማቸዋል።»

ቁጥሩ ሁሉንም ይለዋል።የነዳጅ ዘይት ምርት ከተቋረጠ በሕዋላ የሰሜን ሱዳን ምጣኔ ሐብት ለሁለት ተከታታይ ዓመታት እያሽቆለቀለ ነዉ።በጎርጎሮሳዉያኑ ሁለት ሺሕ አስራ-ሁለት ብቻ በአስራ-አንድ ከመቶ አሽቆልቁሏል።መንግሥት ለነዳጅ ዘይት የሚያደርገዉን ድጎማ በማቋረጡ ለተቃዉሞ አደባባይ የወጣዉ ሕዝብ በተለይም ተማሪዎች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ሲጋጩ ነበር።

የደቡብ ሱዳን ደግሞ ከሰሜንዋም የባሰ ነዉ።የአዲሲቱ ሐገር፥ አዲስ መንግሥት ዘጠና በመቶ በጀቱ የሚሸፈነዉ ከነዳጅ ሽያጭ ነዉ።ነዳጅ የለም፥- ትምሕርት ቤት፥ ሐኪም ቤት፥ መንገድ ሌላም የለም።ከሁሉም በላይ ነዳጁ ናትስዮን እንደሚሉት ለሌላ ትልቅ አላማም ይፈለጋል።ለጦሩ።
                      ድምፅ
«በእኔ ግምት ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ከአራት መቶ ሺሕ በላይ ደሞዝተኞች አሉ።አንድ መቶ ሺሕ ሲቢል የመንግሥት ሰራተኞች ናቸዉ።መደበኛዉ ጦር ሐይል አንድ መቶ ሐምሳ ሺሕ አባላት አሉት።አንድ መቶ ሐምሳ ሺሕ ሚሊሺያዎችም አሉ።ሚሊሺያዎቹ ድሮ ለሰሜን ሱዳን የሚያግዙ ቢሆንም ሠላሙን እንዳያኩ በሚል ደቡብ ሱዳን እንደ ተጠባባቂ ጦር ደሞዝ ይከፍላቸዋል።ደቡብ ሱዳኖች ሠላማቸዉን ለማስከበር እንደ ብልሐት ያዩት ሁሉንም ደሞዝ መክፈል ነዉ።»

YIDA REFUGEE CAMP, SOUTH SUDAN - JUNE 29: A dirt road leads to the border from this aerial photo near Yida refugee camp along the border with North Sudan June 29, 2012 in Yida, South Sudan. Yida refugee camp has swollen to nearly 60,000, as the refugees flee from South Kordofan in North Sudan. The international aid community is struggling to provide basic assistance to the growing population, most have arrived with only the clothes they are wearing. Many new arrivals walked from 5 days up to 2 weeks or more to reach the camp. (Photo by Paula Bronstein/Getty Images)

ድንበሩ

ሁለቱ ሱዳኖች የነዳጅ ዘይት ምርትና ሽያጭ እንዲቀጥል ከመስማማታቸዉ በተጨማሪ በአዋሳኝ ድንበራቸዉ ላይ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ጥብቅ ቀጣና ለመመስረት ተስማምተዋል።ጦራቸዉን ከአዋስኝ ድንበሩ ማንሳታቸዉ ግን ሱዳናዊዉ ምሁር ማግዲ አል-ጊዙሊ እንዳሚሉት የፀጥታ ክፍተት ሊያስከትል ይችላል።
            
«ይሕ በጣም ረጅምና አስቸጋሪ ድንበር ነዉ።የሁለቱ ሐገራት ጦር መንቀሳቀሻ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አማፂ ሐይላት፥ ባንድ ወይም በሌላ ጊዜ ካንዱ ወገነዉ ሌላዉን የወጉ ሸማቂዎች መናኸሪም ጭምር ነዉ።የሁለቱ ወገኖች ስምምነት መሳካቱ የሚለካዉም ሁለቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያዟቸዉን ሐይላት በመቆጣጠር ብቃታቸዉ ነዉ።»

ደቡብ ሱዳን ስምምነቱ ካልተሳከ ሌላ አማራጭ እያማተረች ነዉ።ነዳጅ ዘይቷን በኬንያ እና በጅቡቲ ወደቦች በኩል ወደ ዉጪ ለመለካ ቧምቧ ለመዝርጋት ማቀዷ ባለፈዉ ሳምንት አስታዉቃለች።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ
 

Audios and videos on the topic