የሁለቱ ሱዳኖች መሪዎች ድርድር | አፍሪቃ | DW | 26.09.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሁለቱ ሱዳኖች መሪዎች ድርድር

የድርድሩን ሂደት የተከታተሉ ዲፕሎማቶች እንዳሉት መሪዎቹ አብዛኛዎቹን ልዩነቶቻቸውን አስወግደዋል ። ይሁንና ከሱዳንም ሆነ ከደበብ ሱዳን በኩል ዲፕሎማቶቹ የተናገሩትን የሚያረግግጥ አለመገኘቱን ሮይተርስ ከአዲስ አበባ ዘግቧል ።

(FILE) A file picture dated 19 January 2010 shows Sudanese President Omar el Bashir (R) and First Vice President and President of the Government of Southern Sudan, Salva Kiir Mayardit (L), participating in celebrations marking the 5th anniversary of the signing of the Comprehensive Peace Agreement (CPA) in Yambio, Sudan. Omar el Bashir has won the country's first multiparty elections in 24 years, election officials said on 26 April 2010. The polls are supposed to usher in a new era of democracy in Sudan, which is recovering from a decades-long civil war between the north and south. EPA/TIM MCKULKA - UNMIS - HANDOUT EDITORIAL USE ONLY/NO SALES +++(c) dpa - Bildfunk+++

አል በሽርና ኪር-አምና

የሰሜንና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች አዲስ አበባ ዉስጥ የሚያደርጉት ድርድር ወደ አግባቢ ዉጤት መቃረቡ ተነገረ።የድርድሩን ሒደት የሚከታተሉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እንዳስታወቁት የሁለቱ ሐገራት መሪዎች አብዛኛ ልዩነታቸዉን አስወግደዋል።ሁለቱ ሱዳኖች የድንበር ግዛት ይገባኛል፥ የነዳጅ ዘይት ሐብት ክፍፍል፥ አንዱ የሌላዉን ተቃዋሚ የመደገፍና የዜግነት ጉዳይ ጠብ- ልዩነታቸዉን በሰላም ለማስወገድ የሁለቱ ሐገራት ዲፕሎማቶችና ባለሥልጣናት በተከታታይ ሲደራደሩ ነበር።ካለፈዉ ዕሁድ ጀምሮ ደግሞ ፕሬዝዳት ዑመር ሐሰን አል-በሽርና ፕሬዝዳት ሳልቫኪር ራሳቸዉ አዲስ አበባ ዉስጥ እየተደራደሩ ነዉ።የኢትዮጵያ የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ቀትር ላይ እንዳስታወቁት በመሪዎቹ መሐል ልዩነት ቢኖርም መስማማታቸዉ አይቀርም።

ስምና ዜግነታቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ዲፕሎማት እንዳስታወቁት ደግሞ መሪዎቹ ከመጨረሻዉ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።ሮይተር ዜና አገልግሎት የድርድሩን ሒደት በቅርብ ያዉቃሉ ያላቸዉ ዲፕሎማት እንዳሉት ስምምነቱ ፊርማ ብቻ ነዉ የቀረዉ።የሁለቱ ሱዳኖች ባለሥልጣናትም ሆኑ አደራዳሪዎች ግን ሥለ ድርድሩ ዉጤት እስካሁን በጋራም ሆነ በተናጥል የሰጡት መግለጫ የለም።
ሂደቱን በመከታተል ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ስለ ሁለቱ ሱዳኖች ድርድር የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይንና አንድ የፖለቲካ ተንታኝ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሰ

Audios and videos on the topic