የሀገር ባህል ወግ | ባህል | DW | 03.11.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

የሀገር ባህል ወግ

በአዝናኝና እና በቁም ነገር አዘል ቀልዶቹ የሚታወቀዉን አብርሃም አስመላሽን የለቱ የባህል መድረክ ዝግጅታችን እንግዳ ነዉ። አብርሃም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ራድዮ፤ እንዲሁም በተለያዩ መድረኮች ይዞአቸዉ የሚቀርባቸዉ አዝናኝ እና ቁም ነገር አዘል ቀልዶቹ ጭዉዉቶቹ እና መነባንቦቹ እዉቅናን አስገኝተዉለታል።

አብርሃምን ከስራዎቹ ጋር አለባበሱን አነጋገሩን አና አኳኋኑን በተለያዩ መድረኮች አልያም በቴሌቭዝን ለተከታተለ፤ ገጠር አድጎ ህብረተሰቡን ባህል ጠንቅቆ ማወቁን ይረዳል። እንደ አብርሃም ግን አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀዉ በዝያዉ በመዲና አዲስ አበባ ነዉ። አብርሃም አዲስ አበባ ተወልጄ ባድግም ይላል የባላገሩን ህይወት እና የአነጋገር ዘዪ አዝያዉ ባደኩበት በፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ነዉ የተዋወኩት። አብርሃም ወደ 20 አመት ግድም በኢትዮጳያ ራድዮና ቴሌቭዥን ቁም ነገር አዘል ቀልዶቹን አና መነባንቦችን በማቅረብ በህዝብ ታዋቂነትን ቢያገኝም፤ የሚያገኘዉ ገንዘብ ከመቶ ብር ያነሰ እንደነበር አጫዉቶናል። በባላገሩ የአነጋገር ዘዪ ተሸክፈዉ ቁም ነገሮችን ያዘሉት የአብርሃም ኪነ-ጥበባዊ ስራዎች ትምህርታዊ ቀልዶቹን፤ በተለይ መነባንቦቹን የቋንቋ ምሁራንም ያደንቁለታል። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጳያ ቋንቋዎች እና ባህሎች ተቋም መምህር የሆኑት አቶ አለማየሁ ግሩምን ስለ አብረሃም አስመላሽ ስራዎች ጠይቀናቸዋል። አብረሃም ወደ ኢትዮጳያ ራድዮናቴሌቭዥን ለመጀመርያ ግዜ ወስዶ ስራ ያስቀጠረዉ አብሮ አደግ ጓደኛዉ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴም፤ ስለ አብርሃም ተሰጥዎ አጫዉቶናል። አብርሃም አስመላሽ የጀርባ አጥንት በሽታ፤ ተይዞ አልጋ ላይ ከዋለ አመት እንዳለፈዉ ነግሮናል። እርዳታም ይጠይቃል። በለቱ ቅንብራችን የከያኒ አብርሃም አስመላሽ ስራዎችም ተካተዉበታ። ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 03.11.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16ahr
 • ቀን 03.11.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16ahr