የሀረሪ ክልል ፖሊስ የተሀድሶ ስልጠና ሊወስድ ነው  | ኢትዮጵያ | DW | 15.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሀረሪ ክልል ፖሊስ የተሀድሶ ስልጠና ሊወስድ ነው 

የክልሉ ፖሊስ ሥልጠና በሚወስደበት ወቅትም የክልሉን ሰላምና ፀጥታ የማስጠበቁን ሥራ የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ተክተው እንደሚሰሩ ተገልጿል። የክልሉ ፖሊስ ኃይል በአድሎአዊነት እና የህግ የበላይነትን ባለማስክበር ሲወቀስ ቆይቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:33

የሀረሪ ክልል ፖሊስ በሙሉ የተሀድሶ ስልጠና ሊወስድ ነው

የሐረሪ ክልል ፖሊሶች በሙሉ የተሀድሶ ስልጠና ሊወስዱ ነው። ሥልጠናው በሁለት ዘርፎች ተከፍሎ ለአንድ ወር የሚሰጥ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለDW አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ ሥልጠና በሚወስደበት ወቅትም የክልሉን ሰላምና ፀጥታ የማስጠበቁን ሥራ የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ተክተው እንደሚሰሩ ተገልጿል። የክልሉ ፖሊስ ኃይል በአድሎአዊነት እና የህግ የበላይነትን ባለማስክበር ሲወቀስ ቆይቷል። የድሬዳዋው ወኪላችን  መሳይ ተክሉ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ 

Audios and videos on the topic