ዣን ፒየር ቤምባና የቀረበባቸው የወንጀል ወቀሳ | ኢትዮጵያ | DW | 19.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዣን ፒየር ቤምባና የቀረበባቸው የወንጀል ወቀሳ

ዘ ሄግ ኔዘርላንድስ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት በቀድሞው የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ ምክትል ፕሬዚደንት ጃን ፒየር ቤምባ ላይ ክስ ይመሰርት ይሆን?

ዣን ፒየር ቤምባና

ዣን ፒየር ቤምባ

በቀጣዮቹ ስድሳ ቀናት ውስት ይወስናል። ፍእርድ ቤቱ ዓቃብያነ ህጉ በጦር ወንጀልና በስብዕና ወንጀል በቤምባ ላይ ክስ ይመስርቱ አይመስርቱ በሚለው ማመልከቻ ላይ መወሰን ይቻለው ዘንድ ሰሞኑን የማስረጃዎች ማድመጫ ችሎት አካሂዶዋል። ቤምባ ለኮንጎ ነጻነት የታገለው ቡድናቸው በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፑብሊክ ውስጥ ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ ናቸው በሚል የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ዓቃብያነ ህግ ሰለባዎቹን ካነጋገሩ በኋላ ወቀሳ አቅርበዋል።