ዝክረ ቅዱስ ያሬድ | ባህል | DW | 30.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ዝክረ ቅዱስ ያሬድ

  ኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ለሀገሪቱ የኪነጥበብ ዘርፍ ያበረከተውን ያህል ስሙ ገንኖ አይወራለትም። ሌሎች ባቀናበሩት አንድ ዜማ ስለሙዚቃ በተነሳ ቁጥር ስማቸው በየምክንያቱ የሚጠራ የምዕራቡ ዓለም የጥበቡ ሰዎች በሀገራቸው ብቻ ሳይሆን መላው ዓለም ለሥራቸው ትኩረት ሰጥቶ ያወሳቸዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 16:11

ቅዱስ ያሬድ በጀርመን ሲታወስ

 ከዛሬ 1500 ዓመታት በፊት አክሱም ላይ የተወለደው ቅዱስ ያሬድ፣ በኪነጥበቡ ዘርፍ የዜማ ፈጣሪ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ባለቅኔ እና ገጣሚ፤ በመንፈሳዊው ረገድ ደግሞ ጻዲቅ፣ መናኝ፣ ሰማዕት እና ለሃይማኖቱም ከፍተኛ በረከት ያቀረበ እንደሆነ ምሁራን ይናገሩለታል። ስለያሬዳዊ ዝማሬ ሲነሳ፣ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዕለት ከዕለት መንፈሳዊ አገልግሎት ያበረከታቸው የግዕዝ ፣ ዕዝል እና አራራይ ዜማዎች በየዕለቱ በቅዳሴ፣ በማኅሌት እና ሰዓታቱ አምልኮታዊ ሥርዓቱን ያደምቃል። እንዲህም ሆኖ ግን ቅዱስ ያሬድ ያበርክቶውን ያህል ዝናውን እንዳልገነነለት የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ይናገራሉ።

ስለሥራዎቹ ብዙም በውጭው ዓለም ባለመታወቁም የእርሱ ቅኔዎች ላይ ምርምር ያካሄዱ አንዳንድ የውጭ ምሁራን እንዲህ ያለው የረቀቀ የጥበብ አስተሳሰብ ከኢትዮጵያ ሊሆን አይችልም ማለታቸውንም በጥናታቸው ለማሳየት ሞክረዋል። ይህን በመጥቀስም ስለቅዱስ ያሬድ ገና ብዙ መናገር እና ማስተማር እንደሚገባ ያሳስባሉ። በቅርቡ እዚህ በጀርመን ሀገር ቅዱስ ያሬድን ያዘከረ ጥናታዊ ጽሑፎችም የቀረቡበት መርሃግብር ተከናውኗል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤

እንዳልካቸው ፈቃደ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic