ዝቅተኛ የክፍያ ተመን በአፍሪቃ | ኤኮኖሚ | DW | 09.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

ዝቅተኛ የክፍያ ተመን በአፍሪቃ

አፍሪቃ ውስጥ ሥራ እያላቸውም በልተው ማደር ያቃታቸው ጥቂቶች አይደሉም። እንደ ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት በምህፃሩ ILO መዘርዝር ከሆነ 40 ከመቶ የሚሆን አፍሪቃዊ የሚተዳደረው በቀን ከ25 ብር በታች በሆነ ገቢ ነው።

በቂ ያልሆነ የክፍያ ተመንን ለማስቀረት አንዳንድ አገሮች ቢያንስ ሊከፈል የሚገባዉን የመጨረሻ ዝቅተኛ የክፍያ ጣራ ተምነዉ ተግባራዊ አድርገዋል። የገንዘብ መጠኑ የሚተመነዉም በመንግሥት ነው። አፍሪቃ ውስጥ እንዲህ ያለዉን የደመወዝ ተመን በሥራ ላይ ካዋሉ ሶስት ሀገራት የሁለቱን እንመልከት። በቅድሚያ ታንዛንያ ፦

Babuli Kitwawa Sururu, a manager at Vera Club on the south coast Zanzibar shows beach sun-bathing beds Jan. 25, 2003, lying idol after tourists cancelled their stay at the popular white sand beach hotel because of terror alerts issued by western countries. (AP Photo/ George Mwangi)

ፓጄ ዛንዚባር ደሴት ላይ በስተምስራቅ የምትገኝ ትንሽ መንደር

የውቂያኖሱ ማዕበል ድምፅ፣ በዉሃዉ ዳርቻ ያለው ነጭ አሽዋ እና መልካም አየር በሺዎች የሚቆጠሩ አገር ጎብኝዎችን በየዓመቱ ይስባል። ፓጄ ዛንዚባር ደሴት ላይ በስተምስራቅ የምትገኝ ትንሽ መንደር ናት። ወደዚህ ቦታ የሚመጡ አገር ጎብኝዎች ጠቀም ያለ ገንዘብ ይዘው ይመጣሉ። ሰው በሚበዛበት ሰዓት « በዳሜ» እንግዳ መቀበያ ሆቴል የአንድ ክፍል ዋጋ 2,000 ብር ይደርሳል። አብዛኞቹ ሠራተኞች ደግሞ 1,600 ብር ይከፈላቸዋል። በወር መሆኑ ነው። ይህም እስካሁን በመንግሥት የተበየነው ዋጋ ነው። ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ግን የዛንዚባር የእንደራሴዎች ምክር ቤት ይህንን አነስተኛ የክፍያ ተመን ለማሻሻል ይፈልጋል። ጀርመናዊቷ- ዚና ሀይደማን የዳሜ እንግዳ መቀበያ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ ናቸው። ይህን ሲሰሙ በጣም ነበር የተገረሙት። ጉዳዩ በአግባቡ አልታሰበበትም በዚህ ምክንያት ደግሞ ብዙዎች ከሥራ ሊፈናቀሉ ይችላሉ ባይ ናቸው።

«አንድ ሶስተኛ ወይንም ቢያንስ ቢያንስ ግማሽ የሚሆኑ ሠራተኛቻችንን ከሥራ ማሰናበት ይኖርብናል። ምክንያቱም በተባለዉ መጠን የሚከፍል አቅም የለንም። የደሞዝ ጭማሪው ከፍ ባለ ቁጥርም ከስሥራ የምናሰናብተዉም የሠራተኛ ቁጥር በዚያዉ ልክ ይጨምራል። ይህ ደግሞ የሚያስደስት አይደለም። መንግሥት በአግባቡ አላሰበበትም። በየዓመቱ ወይም በየሁለት ዓመቱ የጭማሪዉን መጠን ከፍ የሚያደርጉ ቢሆን ደህና እንዲህ ባንዴ ሰማይ የሚደርስ ጭማሪ ግን አስቸጋሪ ነው።»

ሀይደማን በአጠቃላይ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን መተመኑን አይቀበሉም። መንግሥት በኢኮኖሚው ላይ ጫና ይፈጥራል ባይናቸዉ። በሌላ በኩል ደግሞ ሀይደማን መንግሥት ይህንን ተመን በማድረጉ በሚያስተዳድሩት ሆስቴል የሠራተኞቹ ደሞዝ ባለፉት 3 ዓመታት በጥፍ መጨመሩን እና እንደዛም ሆኖ ሆቴሉ ትርፋማ እንደሆነ ይገልፃሉ። እንደ ጀርመናዊቷ ከሆነ ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን ትርጉም የሚኖረው በየቦታው በሥራ ላይ ከዋለ ብቻ ነው። እሳቸው እንደሚሉት ተቆጣጣሪዎቹ ሙሰኞች እንደሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ነው። ስለሆነም አንዳንድ ድርጅቶች መክፈል ያለባቸውን ደመወዝዝ በአግባቡ አይከፍሉም።

« ለዚህም ነው የሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስቴር እና መንግሥት የኃላፊነቱን ድርሻ ሊይዙ አይችሉም የምለው። ምክንያቱም ጉቦ ከሰጠህ ነፃ እንደምትሆን ታውቀዋለህ። የሆነ ጥፋት አጥፍተህ ፤ በቂ ገንዘብ ካለህ ነፃ ለመሆን ቀላል ነው። ዛንዚባር ውስጥ ደግሞ ገንዘብ የሚገኘው በቱሪዝም መስክ ነው። ይህን ደግሞ መንግሥት ያውቃል። አንዳንዴ የሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ ህግ ሲወጣ የሚደሰት ይመስላል። ምክንያቱም በዚህ ምክንያት አዲስ ቅጣት እና ግብር ማስከፈል ይችላልና።»

Der Unternehmer Hamed Hassan Aboud in seinem Restaurant in Paje, Sansibar Fotograf: Adrian Kriesch (DW Mitarbeiter, Rechte geklärt) Aufnahmedatum: September 2013

ሀመድ ሀሳን አብዱ አዲስ በከፈቱት ምግብ ቤት

ከእሳቸዉ የእንግዳ ማስተናገጃ ሆስቴል በተወሰነ ሜትር ርቀት ላይ ደግሞ ሀመድ ሀሳን አብዱ አዲስ በከፈቱት ምግብ ቤት ተቀምጠዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ስድስት ሠራተኞች ቀጥረዋል። ሁሉም የሚያውቋቸው ሰዎች እና የቤተሰብ አባላት ናቸው። መንግሥት በቂ የመቆጣጠር አቅም ስለሌለው የምግብ ቤቱ ባለቤት ስጋት የላቸውም። በዛ ላይ የተወሰነዉን ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን የመክፈል አቅሙም የላቸውም። «ይህ በተግባር ላይ ሊውል አይችልም። ለዛውም እንደዚህ ባለች ትንሽ መንደር። ምክንያቱም ብዙ መከፈል ያለባቸው ነገሮች አሉ። ለምሳሌ የመብራት፣ ጋዝ ፣ ማብሰያ የሚሆን ከሰል እና እንጨት,,, እና በትንሽ መንደር ያሉ ሱቆች ምናልባት 30 ዶላር ይከፍላሉ። አንድ አስተናጋጅ ደግሞ በዛ ቢባል 60 እና 55 ዶላር ያገኛል።»

አንዳንዶቹ የሀመድ ሀሳን አብዱ ተቀጣሪዎች በወር የሚያገኙት 650 ብር ነው። ይህ መንግሥት የበየነውን ዝቅተኛ የደሞዝ ተመን ግማሽ እንኳን አይሆንም። ቀጣሪው ግን ከዚህ በላይ ሊከፍሉ እንደማይችሉ ይናገራሉ። ችግሩ አቅርቦት እና ፍላጎት አለመመጣጠኑ ነው። እንደ የዓለም ባንክ መዘርዝር ከሆነ ዛንዚባር ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወጣት የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ነው። በቂ የሥራ እድል ስለሌለም አብዛኛዉ ወጣት ሥራ አጥ ነው። ሰው ዝቅተኛ ክፍያ እየተከፈለው የሚሠራበት ምክንያት ለዚህ እኮ ነው እያሉ አብዱ ያስረዳሉ። አብዛኞቹ የኢኮኖሚ ምሁሮችም ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን ከተደረገ ብዙ ሰዎች ከሥራ ገበታቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ ነው የሚሉት።

ባርባራ ሪድሙለር ግን ይህ ፕሮፓጋንዳ ብቻ ነው ባይ ናቸው። በጡረታ ላይ የሚገኙት ጀርመናዊት የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር በበርሊን ዮንቨርሲቲ ለዓመታት በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት አድርገዋል።

እንደ ምሳሌ የጠቀሱት የባርክሌይ ዮንቨርስቲን ጥናትነው። ጥናቱ እንደሚያሳየው የዮናይትድ ስቴትስ የሥራ ቀጣሪዎች የዝቅተኛ ደመወዝ ተመን በመደረጉ ሠራተኞቻቸውን ከሥራ አላፈናቀሉም። ሪድሙለር ሌላ ምክንያትም ጨምረዋል።

አንድ ሠራተኛ ለኑሮ የሚያስፈልገውን ያህል ደመወሞዝ ተከፍሎት ካልሰራ ለጡረታው ብሎ የሚከፈለው አይኖረዉም፣ ግለሰቡ ይህን ባለመክፈሉም በጡረታው ወቅት የሚያገኘዉ ገንዘብ ያንሳል። ይሁንና መንግሥትም ይሁን የሙያ ማህበራት በአግባቡ ካልሰሩ እድሜ ልኩን አንድ ሰው ከድህነት አይላቀቅም፣ የዝቅረኛ ደመወዝ ተመንም ትርጉም አይኖረውም፤ ይላሉ ወይዘሮዋ። « እስካሁን የነበረውን መለስ ብለን ብንቃኝ በአጠቃላይ ማለት የሚቻለው፤ የሥራ ህግ፣ የደመወዝ ክፍያ እና የመሳሰሉት በትግል የተገኙ እንጂ ከሰማይ የወረዱ አይደሉም። በዛ ላይ ጥያቄዉ የሙያ ማህበራቱ እንዴት ነው የተደራጁት?የሚለዉ ይሆናል። ይህ ደግሞ በአብዛኛው የአፍሪቃ ሀገራት ችግር ነው። ከደቡብ አፍሪቃ በስተቀር በሌላው አካባቢ ያለዉ የተለየ ነው።»

Farmarbeiter der Mgutu Farm trinken aus einem Fluss Foto: Columbus S. Mavhunga, DW, Januar 2012 Titel: Farm workers Zimbabwe Mgutu Farm Aufnahmeort: Mgutu Farm, Mazowe, Simbabwe

በግብርና ሥራ የተሰማሩ ሠራተኞች ክፍያቸው እንዲጨመር በደቡብ አፍሪቃ ሰልፍ በማድረግ ደመዋዛቸውን አስጨምረዋል

በጎርጎሪዮሳዊዉ 2012 መጨረሻ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በግብርና ሥራ የተሰማሩ ዌስትካፕ ውስጥ አደባባይ ወጥተው ነበር። የአንድ ግብርና ባለቤት ሰልፈኞቹ ላይ በመተኮሱም ይበልጥ አመፁ ተባብሶ ቆይቷል። የሰልፉም ምክንያት የዝቅተኛ ደመወዝ ተመን ጉዳይ ነው። ሠራተኞቹ ክፍያቸው በቀን 275 ብር እንዲሆን ነዉ የጠየቁት፤ አንዳንዶቹ 138 ብር ብቻ ነዉ የሚያገኙት። አደባባይ ከወጡት አንዱም ብሶታቸውን ሲገልፁ፤«ስድስት ልጆችና እና ባለቤቴን ጨምሮ እንዴት ብለን ነው በዚች ደሞዝ መተዳደር የምንችለው? እኛ የምናገኘዉን ያህል ገቢ ያላቸዉ ሁሉ እየተራቡነዉ።»

ከዚህ የተቃውሞ ሰልፍ በኋላ የደቡብ አፍሪቃ መንግስት የዝቅተኛ ክፍያ ተመኑን በቀን ወደ 188 ብር ከፍ አፍርጓል። ይህም ሊሆን የቻለው በሙያ ማህበራት ጥረት ነው። ምንም እንኳን በደቡብ አፍሪቃ ያሉት የሙያ ማህበራት ጥቂት ቢሆኑም ደቡብ አፍሪቃ ከአፍሪቃ በዚህ ረገድ የረዥም ዓመታት ታሪክ አላት። በተለይ በማዕድን ማውጫው ዘርፍ የደቡብ አፍሪቃ የሙያ ማህበራት ስም ሲነሳ ሰንብቷል። ፓትሪክ ክራቬን የሀገሪቱ የሙያ ማህበራት ህብረት ቃል አቀባይ ናቸው። የሚሰጡት ምክንያት፤ ሠራተኞቹ በቂ ክፍያ ካገኙ የመግዛት አቅማቸው ይጨምራል በዚህ የተነሳም የምጣኔው ሀብት ያድጋል የሚል ነው። « በህግ የተቀመጡ ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን ባለባቸው ዘርፎች የተቀጣሪዎች ህይወት ይበልጥ ሲሻሻል ተስተውሏል። ይሁንና ደቡብ አፍሪቃ ከዓለም አንጻር ያልተመጣጠነ ተመን እንዳላት ይስተዋላል። ነገር ግን ይህን ዝቅተኛ የክፍያ ተመኑን በማስተካከል ብቻ በጠቅላላው የሚቀየር አይደለም። እንዲያም ሆኖ ገና እታች ላሉት ቢያንስ የሚቀራረብ የኑሮ ደረጃ ያለዉ ማህበረሰብ ለመፍጠር ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል። »

ይህን በመመርኮዝም አለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት በምህፃሩ ILO መንግሥት በጥሞና እንዲያስብበት እና በየጊዜው ክፍያውን እንዲያሻሽል ይመክራል። የድርጅቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ቶጎዋዊው ጊልበርት ሆንጋቦ ዝቅተኛ የክፍያ ተመኑን በተናጥል ብቻ መመልከት አይገባም ይላሉ። « ይልቁንም በአጠቃላይ በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ መቃኘት ያስፈልጋል። የአኗኗሩ ሁኔታ ምን ይመስላል? ለመኖር የሚያስፈልጉት ነገሮች ዋጋስ? የማህበረሰቡ እና የሠራተኛው የጤና ዋስትና የመሳሰሉትስ? ይህ አውሮፓንም ይመለከታል።» በአሁኑ ወቅት ስለ ሠራተኛ ደመወዝ ተመን በመነጋገር ላይ የምትገኘዉ ሀገር ጀርመን ናት። ጉዳዩ ግን በሌሎች የአፍሪቃ ሀገራትም የመነጋገሪያ ርዕስ ነው። የአህጉሩ አንድ ሶስተኛ ሀገራት ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን ነዉ ያላቸዉ። የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሚካኤል ሳታ ከሁለት አመት በፊት ባካሄዱት የምርጫ ዘመቻ የበለጠ ደመወዝ ይከፈላችኋል የሚል መፈክር እንደነበራቸዉ አይዘነጋም። የቤት ሠራተኞች ደመዝ በእጥፉ አድጓል፣ የግብርና ሠራተኞች ደመወዝም እንዲሁ በ4 እጥፍ ጨምሯል።

አድሪያን ክሪሽ

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic