ዝምባብዌና የ SADC መሪዎች ጉባዔ በሉሳካ፧ | አፍሪቃ | DW | 16.08.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ዝምባብዌና የ SADC መሪዎች ጉባዔ በሉሳካ፧

ሉሳካ ዛምቢያ የተጀመረው የደቡባዊው አፍሪቃ የልማት ማኅረሰብ (SADC) የመሪዎች ጉባዔ፧ ከሚነጋግርባቸው ጉዳዮች ዋናው የዝምባብዌው ቀውስ ነው። ባለፈው ጊዜ ዳሬሰላም፧ ታንዛንያ ተሰይሞ የነበረው የ SADC ጉባዔ፧ የዝባብዌን መንግሥትና ተቃዋሚዎችን እንዲያደራድሩ፧ የደቡበ አፍሪቃውን ፕሬዚዳንት ታቦ እምቤኪን መርጦ፧ ድርድሩ ጥሩ አጀማመር ቢያሳይም፧

የዝምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በአንድ የ SADC ጉባዔ ላይ፧

የዝምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በአንድ የ SADC ጉባዔ ላይ፧

መንበሩን፧ ፕሪቶሪያ፧ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ያደረገው የዓለም አቀፍ የስልት ጥናት ተቋም ኀላፊ ዶክተር ጃኪ ሲላስ፧ የዝምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በአቋማቸው እንደጸኑ መሆናቸውን ገለጸዋል። ተክሌ የኋላ፧ ዶክተር ሲላስን አነጋግሮ የሚከተለውን አጠናቅሯል።......
«በሚያስገርም ሁኔታ፧ አዎንታዊ በር መክእፈቱን ነው የምንገነዘበው። በለኆሳስ የሚካሄድ የዲፕሎማሲ ተግባር የተሰኘው የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚዳንት ታቦ እምቤኪ አያያዝ አንዳች ረብ ያለው ውጤት አላስገኘም። ላለፉት ብዙ ዓመታት እምቤኪ ከዝምባብዌ አንጻር ለዘብ ያለ አመራር ዘይቤ መከተላቸው ዕርቀሰላም እንዲወርድ ለመገላገል የሚያስችል ዕድል አለው የሚል ስሜት ፈጥሮ ነበር። የዕርቀ-ሰላሙን ሂደት ሲከታተሉ የቆዩት ወገኖች የደቡብ አፍሪቃ ከ ZANU-PF አንጻር ያላት አቋም እጅግ ተለሳልሶ የቀተለ ነው። የተለወጠ ነገር የለም በማለት ጉዳዩ ሲያሳስባቸው ቆይቷል። ስለሆነም የድርድሩ ሂደት፧ እስካሁን ስምምነት አላማስገኘቱ ድርድሩ ደግሞ እንዲቀጥል ካለ ጽኑ ፍላጎት አኳያ፧ ሁኔታዎች ግልጽ ሆነው መድረክ ላይ መቅረባቸው፧ ዝምባብዌን በተመለከተ፧ ምናልባትይበልጥ በቅንነት ጉዳዩን በጥሞና ለመያዝ የሚያስችል መድረክ ይከፍት ይሆናል።«
የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚዳንት ታቦ እምቤኪ ከደቡብ አፍሪቃ አንጻር ለምን እጅግ የተለሳለሰ አቋም ያዙ? ችግሩ፧ ደቡብ እሪቃን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ይጎንጣታል። ምክንያቱም በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ዝምባብዌአውያን ወደ ደቡብ አፍሪቃ እየተሰደዱ ናቸው፧ ይህ ደግሞ ለዚያች ሀገር ሰክም መሆኑ እሙን ነው።
«እንደሚመስለኝ፧ ለዚህ ብዙ ምክንያቶች አሉ ዋናው ምክንያት ግን፧ ዝምባብዌ ጎረቤት ናት። ደቡብ አፍሪቃ ለዝምባብዌ «ይህ?« መፍትኄ ነው ብላ ለመጫንም ሆነ አገሪቱን ለመውር አትችልም። ደቡብ አፍሪቃ ወደፊት እንድትገፋበት ያላት ብቸኛ አማራጭ ከዝምባብዌ ጋር በጥሞና መምከር ነው። ባለፉት ጊዜያት ZANU-PF እና ፕሬዚዳንት ሙጋቤ ማንኛውንም የውጭ ገላጋይ እንደማይቀበሉ በግልጽ ማስገንዘባቸው የሚዘነጋ አይደአም። ዝምባብዌ፧ በውስጥ አስተዳደርዋ የፈጠረችውን ምሥቅልቅልበብሪታንያ ማላከኳም የሚታወስ ነው። እዚህ ላይ ግምት የሚሰጠው ሌላም ጉዳይ አለ። ፕሬዚዳንት ሙጋቤ ለአካባቢው ጎረቤት አገሮች፧ የተከበሩ አዛውንት መሪ መሆናቸውን ለማስረገጥ ይሻሉ። የዝምባብዌው መሪ፧ ሽምግልና አልቀበልም ካሉ፧ የአካባቢው አገሮች ቀሪና አማራጭ የሆነ ከረር ያለ እርምጃ ለመውሰድ ይገፋፉ ይሆናል። ሌላው የማይረሳው ጉዳይ፧ ዝምባብዌ፧ ለአካባቢው ጎረቤት አገሮች ከቅኝ አገዛዝ መላቀቅ ጠቃሚ ድርሻ ማበርከቷን ማወቅ ተገቢ ይሆናል።
ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ እልህ በመጋባት፧ አገር አቀፉን ዕርቀ-ሰላም ችላ ከማለታቸውም፧ በተቃውሞው ወገን ላይ ጭቆና ማጠንከራቸው ነው የሚነገረው። ሙጋቤ፧ «የፖለቲካ ተሃድሶ ለውጥ አስፈላጊ አይደለም በዓለም ውስጥ እንደሚገኝ እንደማንኛውም ሀገር፧ በዴሞክራሲ ነው የምንመራው« ነው የሚሉት።ዝምባብዌ ሽምግልናውን አያስፈልግም በማለት እንደማጣጣሏ መጠንምን ይከተላል? የደቡባዊው አፍሪቃ አገሮች ኅብረትም ሆነ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ምን ማድረግ ይችላሉ?
«አሁን ይሆናል ተብሎ በተስፋ የሚጠበቀው ዐቢይ ጉዳይ፧ ዝምባብዌ የምታደርገው የጭቆና መጠንና ጭካኔ እንደሚወገዝ ነው። የአፍሪቃ ኅብረትም ሆነ የደቡባዊ አፍሪቃ አገሮች የልማት ማኅበር ምንም ያደረጉት የለም። ዛምቢያና ቦትሳና ብቻ ናቸው የዝምባብዌ ይዞታ እንዳልጣማቸው በግልጽ ያሳወቁ። ደቡብ አፍሪቃ በሚያሳዝን ሁኔታ በዝምባብዌ ስለሚታየው ሁኔታ ዝምታን መምረጧ ታውቋል ሐራሬ አሁን ዕርቀ-ሰላም አለመቀበሏ፧ ደቡብ አፍሪቃ ይበልጥ ገሀዳዊ እርምጃ ትወስድ ዘንድ ይገፋፋ ይሆናል። ይሁንና የአካባቢው አገሮች በዝምባብዌ ላይ እገዳ የሚያስተዋውቁ መሆናቸው በጥርጣሬ ነው የሚታየው።«