ዜና መዕዋል ምንድን ነዉ? | ባህል | DW | 15.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ዜና መዕዋል ምንድን ነዉ?

«በመሰረቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ የነበረዉ እያንዳንዱ ንጉስ በዘመኑ ዜና መዕዋል አለዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜና መዕዋል መጻፍ የተጀመረዉ ከ 14ኛዉ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜና መዕዋል መጻፍ የተጀመረዉ በንጉስ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ነዉ።»

አውዲዮውን ያዳምጡ። 14:58

ጥንታዊ የግዕዝ ጽሑፎች ጥናት


ዶክተር ሰለሞን ገብረየስ ይባላሉ። በጥንታዊ ችሑፎች ጥናት በተለይ ደግሞ በተለይ በግዕዝ ጽሑፎች ጥናት ፤ በአፄ ገላዉድዮስ ዜና መዕዋል ላይ ከሃንቡርግ ዩንቨርስቲ የዶክትሪት ማዕረጋቸዉን በቅርቡ ተቀብለዋል። ይህን የዜና መዕዋል ከግዕዝ ወደ እንጊሊዘኛ ተርጉመዉ በመፅሐፍ መልክ ለመታተምም ዝግጅት ላይ ነዉ ።


በጥንታዊ ግዕዝ ጽሑፎች ላይ ምርምር የሚያደርጉትን ምሁር ዶክተር ሰለሞን ገብረየስ በሰሜናዊ ጀርመን የወደብ ከተማ በሆነችዉ በሃምቡርግ ከተማ በሚገኘዉ ዩንቨርስቲ ነዉ፤ ከሦስት ዓመት ከዘጠኝ ወር ምርምር ፤ ስራና አንድ ከግዕዝ ወደ እንግሊዘኛ የተረጎሙትን ትልቅ መፅሐፍን ለህትመት ከሰጡ በኋላ ከሳምንታት በፊት የዶክትሪት ማዕረጋቸዉን በይፋ የተቀበሉት። በርግጥ የዶክትሪት ማዕረግን ብቻ አይደለም የተቀበሉት ባገኙትም ዉጤት ከፍተኛ ክብር አግኝተዋል፤ ተነግሮላቸዋልልም።

Äthiopien Solomon Gebreyes Beyene

ዶክተር ሰለሞን ገብረየስ

ዶክተር ሰለሞን በታሪክ ትምህርት በማስትሪት ማዕረግ ትምህርታቸዉን ያጠናቀቁት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ነዉ። ከዝያ ነዉ ሞያቸዉን ወደ ጥንታዊ የግፅዝ ጽሑፎች ለማድረግ ወስነዉ ግዕዝን ተምረዉ በዚሁ ዘርፍ ለዶክትሪት ማዕረግ የበቁት፤


በመካከለኛዉ የኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ አፄ ገላዉዲዮስ አልያም ንጉስ ገላዉዲዮስ ዘመን የተፈፀመ ታሪክ የኢትዮጵያ አንዱት ትልቅ ታሪክ መሆኑን ዶክተር ሰለሞን ገብረየስ በዝርዝር ያስረዳሉ።
በኢትዮጵያ በ 14ኛዉ ክፍለ ዘመን በአምደ ጽዮን ዘመን የመጀመርያዉ የዜና መዕዋል እንደተጻፈ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የተለያዩ የግዕዝ ጽሑፎችን በማሳተም የመካከለኛዉ ዘመን ታሪክ ለዓለም የታሪክ ተመራማሪዎች እየተሰራጨ መሆኑንም ዶክተር ሰለሞን ገብረየስ ተናግረዋል።
በጥንታዊ የግዕዝ ጽሑፎች ላይ ምርምር የሚያደርጉትና በቅርቡ የዶክትሪት ማዕረግን ከሃምቡርግ ጀርመን ዩንቨርስቲ የተቀበሉት ዶክተር ሰለሞን ገብረየስን ለሰጡን ቃለ ምልልስ በዶይቼ ቬለ ስም በማመስገን ሙሉ ዝግጅቱን እንዲያደጡ እንጋብዛለን።


አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic