ዚምባብዌና የዘገየው የምርጫ ውጤት | አፍሪቃ | DW | 01.04.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ዚምባብዌና የዘገየው የምርጫ ውጤት

በዚምባባዌ ምክር ቤታዊውና ፕሬዚደንታዊው ምርጫ ከተካሄደ ዛሬ ሶስተኛ ቀን ሆኖታል። ሆኖም፡ የምርጫው ይፋ ውጤት እስካሁን ገና አልወጣም። ይህም ገዢው የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ውጤቱን ለማጭበርበር ያደረገው ነው የተቃውሞ ወገኖች ወቀሳ እያሰሙ ነው። የሀገሪቱ የአስመራጭ ኮሚሽን ህዝቡ ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪ ባቀረበበት ባሁኑ ጊዜ፡ የተቃውሞው ወገንና የውጭ መንግስታት ኮሚሽኑ ውጤቱን በተቻለ ፍጥነት እንዲያወጡ እያሳሰቡ ነው።

የተቃውሞው ወገን ደጋፊዎች

የተቃውሞው ወገን ደጋፊዎች