ዚምባብዌና የኤድስ ግብር | ጤና እና አካባቢ | DW | 17.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ዚምባብዌና የኤድስ ግብር

ዚምባቡዌ ዉስጥ ማንም ስራ ያለዉ ሰዉ የኤች አይቪ ኤይድስን በሀገሪቱ ለመቆጣጠርና ለማጥፋት፤ የታመሙትም ሰዎች ለመርዳት ከወር ደመወዙ ከመቶ ሶስት እጁን በግብር መልክ እንዲከፍል በህግ ተደንግጓል።

በዚህ ገንዘብም አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ የሚጠጉ HIV በደማቸዉ የሚገኝ ወገኖች መድሃኒት ተገዝቶ ይታደላል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በተለይ በገጠሪቱ ዚምባቡዌ የሚገኙ ህመምተኞች መድሃኒቱን ለማግኘት ችግር ገጥሟቸዋል። አሁን ዝም ብለን ብናይ ሞት ሰልፍ ብንወጣ ጥይት በሚል ተሰባስበዉ ማኅበር በማቋቋም አድማ መተዉ ሃራሬ ላይ ሰልፍ መዉጣታቸዉን የጠቀሰዉ የዶቼ ቬለዉ ዮርግ ፖፕዲክ የላከዉን ዘገባ ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic