ዚምባቡዌ ከምርጫ በኋላ | አፍሪቃ | DW | 07.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ዚምባቡዌ ከምርጫ በኋላ

የMDC ሥሌት መረጃዎቹ ሕጋዊ መሠረት ካገኙ የዉጪ ሐይላት በተለይም የአፍሪቃ ሕብረት እና የደቡባዊ አፍሪቃ የልማት ማሕበረሰብ (SADC) በፕሬዝዳት ሙጋቤ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ይጠቅማሉ ነዉ።ከተሳካ አዲስ ምርጫ።

Zimbabwe Prime Minister and leader of the opposition Movement for Democratic Change (MDC) Morgan Tsvangirai speaks at a news conference in Harare, June 13, 2013. Tsvangirai on Thursday rejected a plan by President Robert Mugabe to hold an election on July 31, accusing his rival of breaking the constitution and formenting a political crisis in the southern African nation. REUTERS/Philimon Bulawayo (ZIMBABWE - Tags: POLITICS ELECTIONS)

ቻንግራይ

ባለፈዉ ሮብ ዚምባቡዌ ዉስጥ በተደረገዉ ምርጫ የተሸነፈዉ ንቅናቄ ለዴሞክራሲያዊ ለወጥ (MDC) የምርጫዉን ሒደትና ዉጤት በመቃወም ለፍርድ ቤት አቤት ብሏል።በፕሬዝዳታዊዉ ምርጫ የተሸነፉት ጠቅላይ ሚንስትር ሞርጋን ቻንግራይ እና ፓርቲያቸዉ አዲስ ምርጫ እንዲደረግ ይፈልጋሉ።ፍርድ ቤቱም ሆነ የአካባቢዉ መንግሥታትና ማሕበራት ግን (MDC)nö ፍላጎት የሚያሳካ ብይን መስጠታቸዉ ሲበዛ አጠራጣሪ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ ዳንኤል ፔልስ በዘገበዉ ላይ ተመስርቶ ያጠናቀረዉ ዘገባ አለን።

የዚምባቡዌ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ባለፈዉ ቅዳሜ ይፋ ባደረገዉ ዉጤት መሠረት ጠቅላይ ሚንስትር ሞርጋን ቻንግራይ አይሸነፉ-ሽንፈት ነዉ የገጠማቸዉ።ፕሬዝዳት ሮበርት ሙጋቤ ሥልሳ-አንድ ከመቶ።ቻይንግራይ ሰላሳ-አራት።በምክር ቤት አባላት ምርጫም የዚምባቡዌ የረጅም ጊዜ ገዢ ፓርቲ ZANU-PF MDCን በሰፊ ልዩነት ነዉ-የዘረረዉ።

ከሁለት መቶ አስሩ የምክር ቤት መቀመጫ-የሙጋቤዉ ZANU-PF አንድ መቶ ሥልሳዉን ተቆጣጥሯል።MDC አርባ-ዘጠኝ።ጠቅላይ ሚንስትር ሞርጋን ቻግራይ ምርጫዉን ዉጤት ቅዳሜዉኑ ዉድቅ አድርገዉታል።

epa03808349 A Zimbabwe resident of the high density suburb of Mbare in the capital Harare shows her finger with ink after casting her ballot in presidential elections in Zimbabwe 31 July 2013. Zimbabwe's eighty nine year old president Robert Mugabe is seeking another term after thirty three years in power with his Zanu-PF party whilst Prime Minister Morgan Tsvangirai leader of the Movement for Democratic Change (MDC) hopes to win and prevent this. EPA/AARON UFUMELI

መራጩ«MDC የሐምሌ ሰላሳ-አንዱን ምርጫ ሙሉ በሙሉ ዉቅድቅ አድርጎታል።ሀ.በሒደቱ፥ ለ.የተሐድሶ ለዉጥ ባለመደረጉ-ምክንያት።»

አሁን ደግሞ የMDC ሥራ-አስፈፃሚ ኤዲ ክሮስ እንደሚሉት ፓርቲያቸዉ «ተጭበርብሯል» የሚለዉ ምርጫ ዉጤት ተሰርዞ አዲስ ምርጫ እንዲጠራ በፍርድ ቤት ሊሟገት አቤት ብሏል።

«ፕሬዝዳንታዊዉን ምርጫም፥ ለምክር ቤት አባላት በብዙ ሥፍራ የተሰጠዉን ድምፅም በመቃወም ክስ መስርተናል።ይሕን የምናደርገዉ ትክክለኛ ብይን እናገኛለን ብለን አይደለም።ምክንያቱም ፍርድ ቤቶቹ ራሳቸዉ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይደረግባቸዋልና።ይሁንና ሁሉንም ነገር በሕጋዊ መንገድ ለመረጃነት ለማስቀመጥ ነዉ።»

የMDC ሥሌት መረጃዎቹ ሕጋዊ መሠረት ካገኙ የዉጪ ሐይላት በተለይም የአፍሪቃ ሕብረት እና የደቡባዊ አፍሪቃ የልማት ማሕበረሰብ (SADC) በፕሬዝዳት ሙጋቤ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ይጠቅማሉ ነዉ።ከተሳካ አዲስ ምርጫ።የአካባቢዉ ሐገራት ግን GIGAበሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጣራዉ የጀርመን ጥናት ተቋም ባልደረባ ክርስቲያን ፎን ዞስት እንደሚሉት ዙምባቡዌ የዛሬ አምስት ዓመት ወደነበረበችበት ግጭት እንድትገባ አይፈልጉም።


Eddie Cross is a Member of Parliament for Bulawayo South, a renowned Zimbabwean economist and founder member of the mainstream Movement for Democratic Change party led by Morgan Tsvangirai. He is currently the Policy Coordinator General.

ኤዲ ክሮስ

«የአጎራባች ሐገራት ዓላማ የዚምባቡዌ ሠላም እንዳይታጎል ነዉ።ያሁኑ ምርጫ ስሕተት አለበት ከተባለ የሚኖረዉ አማራጭ አዲስ ምርጫ መጥራት ነዉ።መራጮች ተመዝግበዉ፥ ሁሉም ነገር እንዳዲስ ይደረግ ቢባል ሁከትና ምሥቅል ቅል መፈጠሩ አይቀርም።ይሕን ደግሞ የአካባቢዉ ሐገራት አይፈልጉትም።»

ከአምስት ዓመት በፊት በተደረገዉ ምርጫ ዉጤት ሰበብ የተጫረዉ ግጭት እዚያዉ ዚምባቢዌ ዉስጥ ከሁለት መቶ በላይ ሕይወት አጥፍቷል።ግጭቱን ሽሽት ወደ ደቡብ አፍሪቃ የተሰደዱት ሰወስት ሚሊዮን ሕዝብ ደግሞ ከደቡብ አፍሪቃዉያኑ ጋር ተጋጭቶ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

የMDC ሥራ አስፈፃሚ ኤዲ ክሮስ ፓርቲያችን «ያለፈዉ አይነት ግጭት፥ ወይም የአረብ ሐገራት አይነት ሕዝባዊ አመፅም አይፈልግም ባይ ናቸዉ።

«በየትኛዉም መንገድ ቢሆን ሕዝባዊ ንቅናቄ እንዲኖር አንፈልግም።ይሕን የማንፈልግበት ምክንያት ፀጥታ አስከባሪዎች ሕዝባዊ ንናቄዉን ለመደፍለቅ በኛ ላይ ጠንካራ የሐይል እርምጃ እንደሚወስዱ ሥለምናዉቅ ነዉ።ሕዝባችንን ለዲሕ አይነቱ የግፍ እርምጃ ማጋለጥ አንፈልግም።»

የሮቡ የድምፅ አሰጣጥ ሒደት እብዙ ሥፍራ መሳካር ታይቶበታል።አንዳድ ዘገቦች እንደጠቆሙት ደግሞ ድምፅ ለመስጠት ከተመዘገበዉ ሕዝብ በሰላሳ-አምስት ከመቶ የሚበልጥ ካርድ ታትሞም ነበር።የአፍሪቃ ሕብረት ታዛቢዎች ለችግሩ እንግዳ አይደሉም።የታዛቢዉ ቡድን መሪ የቀድሞዉ የናይጄሪያ ፕሬዝዳት ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ ግን ችግሮቹን «ጥቃቅን» በማለት ነዉ-ያለፏቸዉ።አጠቃላይ ሒደቱንም «ነፃና ፍትሐዊ» ብለዉታል።የሳዴክ የታዛቢዎች ቡድንም ምርጫዉን «ነፃና ሠላማዊ» ነዉ-ያለዉ።

ዩናይትድ ስቴትስ፥ ብሪታንያና ጀርመን ግን የምርጫዉን ሒደትና ዉጤት አሳሳቢ ብለዉታል። ያለፈዉን ይደገማል ብለዉ የሚፈሩት አፍሪቃዉያኑ ግን ጉዳዩን በጥንቃቄ መያዙን ነዉ-የመረጡት።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠAudios and videos on the topic