ዘ ሄግ፤ ICC ዣን ፒየር ቤምባ ላይ የ18 ዓመት እሥራት ፈረደ | አፍሪቃ | DW | 21.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ዘ ሄግ፤ ICC ዣን ፒየር ቤምባ ላይ የ18 ዓመት እሥራት ፈረደ

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ICC በዛሬዉ ዕለት በቀድሞዉ የዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ምክትል ፕሬዝደንት ላይ የ18 ዓመት እሥራት ፈረደ።

የ53 ዓመቱ ዣን ፒየር ቤምባ ባለፈዉ መጋቢት ወር ነበር በቀረቡባቸዉ አምስት የጦር ወንጀል እና በሰብዓዊ ነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚጠቅሱ የክስ ጭብጦች ጥፋተኛ የተባሉት። የኮንጎ ነፃ አዉጭ ንቅናቄ የተሰኘ የግላቸዉ ጦር እንዳላቸዉ የሚነገረዉ ቤምባ፤ ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2002 እስከ 2003ዓ,ም ድረስ ይህን ጦር ወደ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ በመላክ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሞክረዋል የሚል ክስም ቀርቦባቸዋል። የICC አቃቢያነ ሕግ በተለይ አስገድዶ መድፈርን እንደጦር ስልት እንዲጠቀሙ አድርገዋል በማለት ክስ የመሠረቱባቸዉ ቤምባ ቢያንስ 25ዓመት እንዲፈረድባቸዉ ነበር የጠየቁት። ሆኖም የፍርድ ቤቱ ዳኛ ሲልቪያ ሽታይነር ቤምባ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ ፣ የጭካኔ ግድያ እና ርህራሄ የራቀዉ ዘረፋ የፈጸመ ጦራቸዉን መቆጣጠር እንዳልቻሉ በመጥቀስ በአጠቃላይ ፍርድ ቤቱ 18 ዓመት እንደፈረደባቸዉ ገልጸዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ