ዘጋቢዎችን ያሰረችዉ ጅቡቲና ፕረስ | ኢትዮጵያ | DW | 15.06.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዘጋቢዎችን ያሰረችዉ ጅቡቲና ፕረስ

የጅቡቲ መንግስት መቀመጫዉን አዉሮጳ ላደረገ የተቃዋሚ ራዲዮ የወሬ ምንጭ የሆኑ ስድስት ሰዎችን ማሰሩን ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የተሰኘዉ ለጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ተቋም አስታወቀ።

default

ተቋሙ ላለፉት አራት ወራት ጋቦዴ በተሰኘዉ ወህኒ ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ ያላቸዉ የላቩዋ-ደ ጅቡቲ የወሬ ምንጮች ፍርድ ቤትም እንዳልቀረቡም አመልክቷል። የመገናኛ ብዙሃኗ በባለስልጣናት ቁጥጥር ስር መሆናቸዉ የሚነገርላት ጅቡቲ በየካቲት ወር የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ ጎልቶ ታይቶባታል። ሸዋዬ ለገሠ የድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የአፍሪቃ ክፍል ኃላፊ አምብሯዝ ፒየርን አነጋግራ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic