ዘረኝነት ቦታ የለዉም! | ዓለም | DW | 28.08.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ዘረኝነት ቦታ የለዉም!

ባለፈዉ ሳምንት የተጠናቀቀዉ የበርሊኑ 12ኛዉ የአለም አቀፍ የአትሊቲክስ ዉድድር ላይ ከደቡብ አፍሪቃ የ 800 መቶ ሜትር ሩጫ የሴቶች የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ካስተር ሤሜንያ ወንድ ትሁን ሴት የጾታ ክርክር አስነስቶ ስፖርተኛዋ ምርመራ እንድታካሂድ አዘጋጁ አለም አቀፍ የአትሊቲክስ ፊዲሪሽን ማህበር በአዘዘዉ መሰረት ምርመራዉ ተካሂዶአል።

default

ደቡብ አፍሪቃዊቷ ካስተር ሲሜንያ


ባንጻሩ ስፖርተኛይቱ የወርቅ ሜዳሊያዋን ይዛ አገሩዋ ስትገባ የደቡብ አፍሪቃዉ የስፖርት ፊደሪሽን ጉዳዩን የዘረኝነት ሁኔታ ነዉ እንጂ የተጠቀሰዉ ነገር ትክክል አይደለም ሲል ወቀሳዉን ወደ ጀርመን አሰምተዋል። ሁኔታዉ ወደ ዘረኝነት ፊቱን መለወጡ ያሳዘናቸዉ እስፖርተኛዋ ምርመራዉን እንድታካሂድ ያዘዘዉ የዉድድሩ አዘጋጅ የአለም አቀፍ የአትሊቲክስ ፊዲሪሽን ማህበር ዋና ሃላፊ አፍሪቃዊ ትዉልድ ያለዉ ነዉ፤ በተጨማሪ ምርመራ እንድታካሂድ መታዘዙ ያለ ጉዳይ ነዉ ሲሉ ዉንጀላዉን አጣጥለዉታል። በዚህ ጉዳይ ዙርያ የዶቸ ቤለዉ ሉድገር ሻዶምስኪ ሃተታ ጽፎአል ይልማ ሃይለሚካኤል እንዲህ ተርጉሞታል።

ይልማ ሃይለሚካኤል፣ አዜብ ታደሰ፣

ሂሩት መለሰ