ዘረኝነት በብሪታንያ እየከፋ ነዉ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 30.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ዘረኝነት በብሪታንያ እየከፋ ነዉ

ጥቁሮቹ ወይም የአናሳ ዝርያ ተወላጆች ትምሕርት፤ ሥራ፤ፍትሕና የጤና አገልግሎት ለማግኘት ያላቸዉ ዕድል ከነጮቹ ጋር ሲነፃፀር እጅግ ጠባብ ነዉ።ተመሳሳይ የትምሕርት ደረጃ ባላቸዉ ጥቁሮችና ነጮች መካከል ያለዉ የክፍያ ልዩነትም 23 በመቶ ይደርሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:49

ዘረኝነት በብሪታንያ እየከፋ ነዉ

የብሪታንያ ጥቁሮች እና ሌሎች አናሳ ዝርያ ያላቸዉ ዜጎች በቆዳ ቀላማቸዉና በዘራቸዉ ምክንያት የሚደርስባቸዉ በደል ባለፉት ዓምስት አመታት ዉስጥ እየከፋ መምጣቱን በቅርቡ ይፋ የሆነ ጥናታዊ ዘገባ አጋለጠ።በጥናቱ መሠረት የጥቁሮችና የሌሎች አናሳ ዝርያ ያላቸዉ የብሪታንያ ዜጎች ኑሮ ከነጮቹ ጋር ሲወዳደር እጅግ የከፋ ነዉ።ጥቁሮቹ ወይም የአናሳ ዝርያ ተወላጆች ትምሕርት፤ ሥራ፤ፍትሕና የጤና አገልግሎት ለማግኘት ያላቸዉ ዕድል ከነጮቹ ጋር ሲነፃፀር እጅግ ጠባብ ነዉ።ተመሳሳይ የትምሕርት ደረጃ ባላቸዉ ጥቁሮችና ነጮች መካከል ያለዉ የክፍያ ልዩነትም 23 በመቶ ይደርሳል።

ሐና ደምሴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic