ዓ/አቀፍ የርዳታ ጥሪ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች | ኢትዮጵያ | DW | 22.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዓ/አቀፍ የርዳታ ጥሪ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች

ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት ሸሽተው በኢትዮጵያ የሚገኙ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች ለአሳሳቢ የምግብ እጥረት ችግር መጋለጣቸው ተሰማ። ይህን ያስታወቁት የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መስሪያ ቤት፣ ዩኤንኤችሲአር እና የዓለም የምግብ ድርጅት፣ ዳብልዩኤፍ ፒ ናቸው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:29

«ስደተኞች አስቸኳይ ርዳታ ያስፈልጋቸዋል።»

ይህ አሳሳቢ ሁኔታ የከፋ ችግር እንዳያስከትል በሚል እነዚሁ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች  ለነዚህ ስደተኞች ምግብ ለማቅረብ የሚያስችላቸው ሰማንያ ሚልዮን ዩኤስ ዶላር ርዳታ በቀጣዮቹ አስር ቀናት እንዲቀርብላቸው ለለጋሽ ሀገራት ጥሪ አስተላልፈዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic