ዓምደኛ ዳንኤል ብርሃኔ | ባህል | DW | 20.07.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ዓምደኛ ዳንኤል ብርሃኔ

ሀሳብን በነፃ መግለፅ ኢትዮጵያ ውስጥ ተፅዕኖ እንደሚደረግበት የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሚገልፁበት በአሁኑ ወቅት አምደኖች ምን አይነት ተሞክሮ አላቸው?

ዳንኤል ብርሃኔስ ብሎግ የዛሬው የወጣቶች ዓለም የመወያያ ርዕስ ነው።ዳንኤል ከሁለት አመት በፊት የመሰረተው የድረ ገፅ አምድ አለው። ወጣቱ በተለያዩ የምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ጉዳይ ላይ በእንግሊዘኛ  ቋንቋ ይፅፋል።  በአዲስ አበባ የሚኖረው አምደኛ፤ መፃፍ የሚያዘወትረው በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ነው። ኢትዮጵያን በተመለከተ ስለ ሰብዓዊ መብት፣ ስለ የመሬት መቀራመት ስለ ረሀብ እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይፅፋል። ይህን የመረጠበትን ምክንያት አካፍሎናል።

ዳንኤል ብርሃኔስ ብሎግ በሚለው አምዱ ላይ ከዳንኤል ሌላ ነዋሪነታቸው በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የሆኑ ሶስት አምደኞች አልፎ አልፎ ይሳተፋሉ። ዳንኤልን ለመፃፍ ምን እንዳነሳሳው፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ስለሚያሰባስበው የህዝብ አስተያየት፣ ያንድ ወገን ያደላ ፕሮፓጋንዳ ነው የሚፅፈው ስለመባሉም ያጫወተን አለ።

የዳንኤል ብርሃኔ አንባቢዎች በብዛት በኢትዮጵያ እና ሰሜን አሜሪካ እንደሚገኙ በፊስቡክ ገፁ ላይ ይታያል። በኢትዮጵያ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ውስንነት ስንመለከት ምን ያህሉ ሰው ፁሁፎቹን በኢንተርኔት የመከታተል እድል አላቸው? ለዚህስ ወጣቱ ምን ያደርጋል?

ኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት ውስንነት አንዱ ችግር ሆኖ ሳለ በአሁኑ ሰዓት ሀሳብን በነፃነት መግለጽ ያለመቻሉ ሁኔታ እንደ ሌላኛው ችግር ይነሳል።

ለምሳሌ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በፖለቲከኞችና በጋዜጠኞች ላይ ያሳለፈውን ብይን ሽሮ የፈረደባቸዉን  ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን በነፃ እንዲለቅ  የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ሳምንት ጠይቋል። እንደ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ እሪዮት አለሙ የመሳሰሉ አምደኞች በዕስር ላይ ይገኛሉ።  ታድያ በፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ጋዜጠኞች ፤ አምደኞች ለአመታት የዕስር ብይን በተፈረደባቸው በአሁኑ ሰዓት ይህ በአምደኛ ዳንኤል ስራ ላይ ተፅኖ ይኖረው ይሆን? የሚያሰጋውስ ነገር አለ? ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic