1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓመታዊ የንብረት ግብር ከፍያ ረቂቅ አዋጅ በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ መስከረም 18 2016

የንብረት ግብር ወይም «ፕሮፐርቲ ታክስ» አንድ ግለሰብ ወይም ተቁዋም ለሚገለገልበት ንብረት በየዓመቱ ለመንግስት የሚከፍለው የግብር ገንዘብ ነው ። ይህን በተመለከተ አዲስ ረቂቅ አዋጅ በገንዘብ ሚንስትር አማካኝነት ቀርቧል ።

https://p.dw.com/p/4WxMf
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የአዲስ አበባ ከተማ ከፊል ገጽታ፦ ኢትዮጵያምስል Seyoum Getu/DW

ነዋሪዎች የቤት ኪራይ አማሯቸዋል

የንብረት ግብር ወይም «ፕሮፐርቲ ታክስ» አንድ ግለሰብ ወይም ተቁዋም ለሚገለገልበት ንብረት በየዓመቱ ለመንግስት የሚከፍለው የግብር ገንዘብ ነው ። ይህን በተመለከተ አዲስ ረቂቅ አዋጅ በገንዘብ ሚንስትር አማካኝነት ቀርቧል ። ይህ ረቂቅ አዋጅ ባለንብረቶች በሚኖሩበት ቤት እና ቦታ በየዓመቱ የሚያወጡት ዋጋ ተሰልቶ የወለል እና የጣራ  ዋጋ በመተመን ቀመር የሚያስቀምጥ ረቂቅ አዋጅ ነው ። የመዲናዋ ነዋሪዎች ሌላው ቀርቶ ቤት ኪራይ ጭማሪ እንኳን አማሮናል ይላሉ ። ለማን አቤት እንደሚባልም አይታወቅም ሲሉም ምሬታቸውን ለዶይቸ ቬለ (DW) ገልጸዋል ። 

የንብረት ግብር ወይም «ፕሮፐርቲ ታክስ» ምንድን ነው?

ኢትዮጵያ ሕዝብ እንደራሴዎች እና የፌዴሪሽን ምክርቤት የቤት ንብረት ግብርን በተመለከተ አዲስ የሕግ ማእቀፍ እንዲዘጋጅ በወሰናው መሰረት ረቂቅ አዋጁ በገንዘብ ሚንስትር አማካኝነት ቀርቧል ። የንብረት ግብር ወይም «ፕሮፐርቲ ታክስ» በመባል የሚታወቀው አንድ ግለሰብ ወይም ተቁዋም ለሚገለገልበት ንብረት በየዓመቱ ለመንግስት የሚከፍለው የግብር ገንዘብ ነው ። ይህ ግብር ዓመታዊ የንብረት ዋጋ ጭማሪ ላይ ተመስርቶ ንብረቱ በወቅቱ በሚያወጣው ዋጋ ተሰልቶ የሚተመን ይሆናል ።

አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
ሕንጻዎች እና ተሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ፤ ኢትዮጵያምስል Solomon Muchie/DW

የዓመታዊ የቤት ንብረት ዋጋን የሚያወጣው ረኢቅ አዋጅ  በገንዘብ ሚንስቴር ቀርቧል ። የንብረት ግብር ወይም ፕቶፐርቲ ታክስበመባል የሚታወቀው አንድ ግለሰብ ወይም ተቋም ለሚጠቀምበት ንብረት በየአመቱ ለመንግስት የሚከፍለው ገንዘንብ ነው ። ይህ ግብር ዓመታዊ የንብረት ዋጋ ጭማሪ ላይ ተመስርቶ ንብረቱ በሚያወጣው ዋጋ ተሰልቶ የሚተመን  ነው ።

ባለሞያዎች ስለዚህ የግብር አይነት ምን ይላሉ?

ዶይቸ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የመዋለ ንዋይ ባለሞያ ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ  አስተያየት ሰጥተዋል ። ጥናቱን አድርጎታል የተባለው የገንዘብ ሚንስትር ረቂቅ አዋጁን መሰረት በማድረግ ባውጣው ተመን የንብረት ግብር የሚከፍልበትን ዝቅተኛ እና ከፍተኛውን ጣሪያ የገንዘብ መጠን አስቀምጧል ። ዓመታዊ ግብሩ  የሚጣልበት ንብረት የሚሰላው ንብረቱ በወቅቱ  በሚኖረው የገበያ  ዋጋ  መሰረት ተሰልቶ ሲሆን  በዚህ ቀመር  ንብረቱ ከሚያውጣው ጠቅላላ ዋጋ ውስጥ 25  ከመቶ የሚሆነውን መሰረት በማድረግ ነው ተብሏል።

አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
የመዘጋጃ ሕንጻ በአዲስ አበባ ከተማ፤ ኢትዮጵያ ። ከፊት ለፊቱ አዲስ አበባ የሚል በእንግሊዝኛ ፊደላት የተቀረጸ ጽሑፍ ይታያል ።ምስል Seyoum Getu/DW

ነዋሪዎች የቤት ኪራይ አማሯቸዋል

ዜጎች ግብር ከፍለው ለፍተው ባገኙት ገንዘብ የሚሠሩት ቤት ላይ የሚጣለው ግብር  መሰረታዊ የሆነ ጫና አይፈጥርም ወይ በሚል ለቀረበው ጥያቄ  አቶ ተፈራ ያብራራሉ ። የገንዘብ ሚንስቴር ይህንን ተመን ሲያወጣ ከግምት ውስጥ አስገብቼዋለሁ ያለው ንብረቱ ከተፈራ በኋላ በሚጨምረው ዋጋ ላይ ብቻ የተመሰርተ ግብር ለመጣል በማስብ ነውም ብለዋል ። በሁሉም ክልሎች ተመጣጣኝ የግብር ተመን እንዲኖር ያስችላል የተባለበት አዲሱ የግብር መጠየቂያ ረቂቅ  የፌደራል መንግስት ሳይሆን ክልሎች የሚያስተዳድሩት ይሆናል ተብሏል።

የአዲስ አበባ መስተዳድር በየወረዳው ያሉትን የቤት ንብረት አይነቶች ቆጠራ እና ምዝገባ ከጀመረ ሰነባብቶዋል ። የመዲናዋ ነዋሪዎች ቤት ኪራይ ጭማሪ አማሮናል ለማን አቤት እንደሚባልም አይታወቅም ሲሉ ለዶይቸ ቬለ (DW) ምሬታቸውን ገልጸዋል ። 

ሐና ደምሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር