ዓመታዊዉ ዓለማቀፉ የበጎ ፈቃደኞች ቀን | የጋዜጦች አምድ | DW | 05.12.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

ዓመታዊዉ ዓለማቀፉ የበጎ ፈቃደኞች ቀን

በያመቱ ህዳር 19 የበጎ ፈቃደኞች ቀን ተብሎ ይታሰባል። በተለይ እዚህ ጀርመን አገር በልዩ ልዩ ሞያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች በተለያየ ዘርፍች፣ የበጎ አድራጎት ተግባር ያከናዉናሉ

ይኸዉም አንዳንዶች በበሽታ የሚሰቃዩትን ህሙማን ይጠይቃሉ፣ ሌሎች በስፖርት የተደራጁ ወጣቶችን በስልጠና ይረዳሉ፣ እንዲሁም ስደተኛ ልጆች፣ የትምህርት ድጋፍ በመስጠት ፣ የቤት ስራን በማሰራት ፣ በማስጠናት ያግዛሉ። ዛሪ ታስቦ የዋለዉን የበጎ ፈቃደኞች ቀን ምክንያት በማድረግ የኮለኝ ነዋሪ የሆኑትን የአንዲት በጎ ፈቃደኛ ቃለ ምልልስ ያካተተዉን ዘገባ አዜብ ታደሰ አጠናቅራለች።


የቀድሞዋ የዶቸ-ቬለ ጋዜጠኛ የአሁኑዋ ጡረተኛ Irene Meurer የኤርትራ ተወላጅ እና የአስራ ሰባት አበት ወጣትዋን የአስማይድ መለየሱስን ትምህርቷን በማስጠናት’ የቤት ስራ አብሮ በመስራት እየረዷት ይገኛሉ። አስማይድ መለየሱስ በኮለኝ ነዋሪ ናት። ወ/ሮ ሞይረር ኤርትራዊቷን ወጣት የሚያቋት እና እርዳታቸዉን ለወጣቷ መለገስ ከጀመሩ ሶስት አመታትን አስቆጥረዋል። ዜኖ እየተባለ በሚታወቀዉ በኮለኝ ከተማ የሚገኘዉ ወጣት ተማሪዎችን በትምህርታቸዉ ድጋፍ እና እርዳታ የሚሰጠዉ ማህበር ከ 50 በላይ የሚሆኑ የወ/ሮ ሞይረር አይነት በጎ አድራጊዎች የተደራጁነት ሲሆን ማህበሩ ለአንድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ላሉ ተማሪዎች የትርፍ ግዜ የትምህርት ድጋፍ ይሰጣል። ለተማሪዎቹ እርዳታ ለምሳሌ ፣ከባድ በሆነ የቤት ስራ፣ በአንዳንድ የምርምር ስራ፣ ለአንዳንድ መስራቤቶች የሚላክ የትምህርትም ሆነ የስራ ልምድ ለማግኘት ለሚደረገዉ የማመልከቻ አጻጻፍ እርዳታ፣ ባጠቃላይ ለወጣት ተማሪዎች እገዛ፣ ለአንዳንድ ዉይይቶች እና ጥያቄዎች መፍቻ መድረክ ማለት ነዉ። ከፍተኛ ሃላፊነት በተሞላበት በጋዜጠኝነት ሞያ ያገለገሉት የ64 አመት አዛዉንቷ ለ ወ/ሮ ሞይረር አሁን በጡረታቸዉ ይህንን ወጣት ተማሪዎችን ለትም’ህርታቸዉ እገዛ እየሰጡ ያሉበት ተግባራቸዉ በጣም አስፈላጊነት እንዳለዉ ነዉ የሚያምኑበት...

«አንድ ሰዉ ለራሱ ብቻ መኖር የለበትም! እኔ ደግሞ ከወጣቶች ጋር መስራት በጣም እወዳለሁ። አዎ! እዚህ ላይ፣ ይህ እኔ እርዳታ እያደረኩበት ያለዉ፣ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ደግሞ፣ ተማሪዎቹ፣ በጣም እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ ናቸዉ። ታድያ ዋጋ ሊሰጠዉ የሚገባዉ፣ ት/ቤቱ፣ ህጻናቱ እርዳታ እንዲያገኙ እድል መክፈቱ ነዉ። ይህን በእዉነቱ በጣም ጥሩ ነገር ነዉ!»

ወ/ሮ ማወር ለትምህርት ቤቱ ማለት ለተማሪዎቹ ለሚያደርጉት እርዳታ ፍንካች ሳንቲም አይቀበሉም ሙሉ በሙሉ በገዛ ፈቃዳቸዉ በዚህ መልኩ በጎ ድራጎታቸዉን እየለገሱ ነዉ። በጀርመን አገር 36 በመቶ የተለያየ የሞያ ዘርፍ፣ በእንዲህ አይነት የበጎ አድራጊዎች እርዳታ እንደሚተገበር የመዘርዝር ዉጤቱ ያሳያል። በጀርመን ትልቁ ክፍለ ሃገር በኖርድ ራይን ቬስት ፋልያ በርካታ የጀርመን ህዝቦች በተለያየ ዘርፍ በጎ አድራጎታቸዉን እንደሚለግሱ ሲታወቅ ቀጠል አድርጎ በባድን ቩተን በርግ እና በባቫርያም ግዛት እንዲሁ በርካታ ህዝብ እንዳለ ነዉ ዝርዝሩ የሚያሳየዉ። ታድያ ያን ያክልም በርካታ ህዝብ በጀርመን በጎ አድራጎቱን ይለግሳል ቢባልም በአሜሪካ እና በእንጊሊዝ ሚታየዉ ጠንካራ የበጎ አድራጎት ተግባር በጀርመን አይታይም።

ተዛማጅ ዘገባዎች