ዓለም ዓቀፍ የፀጥታና ልማት ጉባኤ በስቶክሆልም | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 13.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ዓለም ዓቀፍ የፀጥታና ልማት ጉባኤ በስቶክሆልም

በእንግሊዘኛው ምህፃር SIPRI በመባል የሚጠራው የስቶክሆልም ዓለም ዓቀፍ የሰላም ምርምር ተቋምና የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ ባዘጋጁት በዚህ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ25 ሃገራት የተውጣጡ የ85 ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል ።

በዓለማችን ሰላምና ልማት ፈተናዎች እንዲሁም መፍትሄዎቹ ላይ ያተኮረ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ ለሁለት ቀናት ተካሄደ ። የተለያዩ ሃገራት ፖሊሲ አውጭዎች ፣ ተመራማሪዎች ና ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ወገኖች በተሳተፉበትና ትናንትናና ዛሬ በተካሄደው በዚሁ ጉባኤ የችግሮቹን ምንጭ ለይቶ በማውጣት በዓለማችን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ላይ ውይይት ተደርጓል ። በእንግሊዘኛው ምህፃር SIPRI በመባል የሚጠራው የስቶክሆልም ዓለም ዓቀፍ የሰላም ምርምር ተቋምና የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ ባዘጋጁት በዚህ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ25 ሃገራት የተውጣጡ የ85 ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል ።ጉባኤው ትናንት ከመከፈቱ አስቀድሞ የስዊድን የልማት ሚኒስትር ኢዛቤል ሎቪንና የጉባኤው አዘጋጆች የሰጡትን መግለጫ የተከታተለው የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴድሮስ ምህረቱ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ቴድሮስ ምህረቱ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic