ዓለም አቀፍ ፀረ የሞት ቅጣት ቀን እና ጋምቢያ | አፍሪቃ | DW | 10.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ዓለም አቀፍ ፀረ የሞት ቅጣት ቀን እና ጋምቢያ

ፀረ የሞቱ ቅጣት ቀን ዛሬ ለ 10ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ ውሏል። በያመቱ የሞቱ ቅጣት በይፋ የሚወገዝበት ይህ ዕለት ታስቦ እንዲውል ሀሳቡን እአአ በ2002 ያነቃቃው የዓለም ፀረ ሞት ቅጣት ጥምረት ነበር።

አላማው ሰዎች በፍርድ የማይገደሉባት አለም ለመፍጠር ታስቦ ነው። ዛሬ ምንም እንኳን በርካታ አገሮች ራሳቸውን ከሞት ፍርድ ቢያገሉም በአለም ዙሪያ 57 ሀገሮች የሞት ቅጣትን አላስወገዱም። ምንም እንኳን ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ጋምቢያ እአአ ከ1981 ወዲህ የሞት ቅጣት ብይን አሳልፋ ባታውቅም፣ ባለፈው ነሀሴ ወር መጨረሻ በሀገርዋ የተፈፀመው ግድያ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ብርቱ ቁጣ ነበር የቀሰቀሰው።

እንደ አምንስቲ ኢንተርናሽናል መዘርዝር በአሁኑ ጊዜ ወደ 20 000 የሚጠጉ ሰዎች የሞት ብይን ተፈርዶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። አፍሪቃ ውስጥ ከ54 አገሮች 38ቱ የሞት ቅጣት ቀርቶዋል።

FILE - In this June 30, 2011 file photo, Gambian President Yahya Jammeh stands outside the Sipopo Conference Center in Malabo, Equatorial Guinea, ahead of the opening session of the 17th African Union Summit. A movement to coronate President Jammeh as King of Gambia may have lost steam, but this ruler of 17 years who claims he can cure AIDS and infertility is all but certain to remain in power after a Thursday, Nov. 24, 2011 presidential vote. (Foto:Rebecca Blackwell, file/AP/dapd).

የጋምቢያ ፕሬዚደንት ያህያ ጃሜ

በፕሬዚዳንት ያህያ ጃሜ አገዛዝ ስር የምትገኘዋ ጋምቢያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚታይባት ሀገር ሆና ብትታወቅም ባለፈው ነሀሴ መጨረሻ በእስረኞች ላይ የሞቱን ቅጣት መፈፀምዋ ብዙ ትችት መቀስቀሱን የዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል የጋምቢያ ተንታኝ ሊዛ ሼርማን ኒኮላውስ ሲገልጹ። « ሰዎች በፖለቲካ ዘርፍ ስህተት ከሰሩና በሀገር ክህደት ከተወነጀሉ የሞት ቅጣት ይበየንባቸዋል። ይህ የአለም አቀፉን መመሪያን እጥሳል። ስለ ቁም ስቅል እና ሀሳብን በነፃ በመግለፅ ላይ ጭቆና እንደሚደረግ ሰምተናል። ስለሆነም እኛን የሚያሳስቡን በርከት ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመለከቱ ችግሮች አሉ።»

እአአ በ 1994 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የጨበጡትፕሬዚዳንት ያህያ ጃሜ ከዚያን ወዲህ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት ይጥራሉ። እስረኞች «ማይል ቱ ሴንትራል» በተባሉ ጣቢያዎች ይታሰራሉ። ይህ ራሱን የቻለ የሞት ቅጣት ነው ይላሉ ባንካ ማኔ፤ ከሰባት የጋምቢያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የተውጣጣ የሲቪክ ድርጅት ሊቀመንበር ናቸው።

A Chinese paramilitary officer keeps the head of a drug dealer bowed during a public sentencing to mark International Day against Drug Abuse and Illicit Drug Trafficking in Hangzhou, eastern China's Zhejiang province, Monday, June 26, 2006. Chinese drug control officials said Thursday their yearlong war on drugs has severely squeezed heroin supplies from the Golden Triangle. Officials also announced the arrest of some 46,000 drug suspects and the seizure of some 6.9 tons of heroin last year. During the trial in Hangzhou, 20 drug dealers were sentenced today with three given the death penalty and executed soon after. (AP Photo) ** CHINA OUT **

በአለም ዙሪያ 57 ሀገሮች የሞት ቅጣትን አላስወገዱም።ቻይና አንዷ ናት።

« የማይል ቱ ወህኒ ቤት የእስራት ሁኔታ አሰቃቂ ከመሆኑ የተነሳ አንድም እዛው ወህኒ ቤት እንዳለህ ፣ አልያም እስራቱ ባስከተለብህ ጉዳት ትሞታለህ። አብዛኛውን ጊዜ ወይ በወታደሮች ወይንም በፀጥታ አስከባሪዎች ላይ ነው የሞት ቅጣት ወይም የዕድሜ ልክ እስራት የሚበየነው። የወህኒ ቤቱ አሰራር ይህን ይመስላል። የሚቀርበው ምግብ እጅጉን የተበላሸ በመሆኑ፣ ቤሪቤሪ የተባለ በሽታ ይይዝህና ሰውነትህ አብጦ እጅግ አስከፊ አሟሟት ትሞታለህ።»

Dyamond Alexander, sister of Johnny Ray Conner, is consoled by James Alexander, after hearing of the execution of Johnny Ray Conner, Wednesday, Aug. 22, 2007, at the Huntsville Unit in Huntsville, Texas. The Texas execution was the 400th in the United States' most active death penalty state since the U.S. Supreme Court allowed capital punishment to resume in 1976. (AP Photo/Paul Zoeller)

የሞት ፍርድን የሚቃወሙ በቲክሳስ ዩናይትድ እስቴትስ

በነሃሴ መጨረሻ ከተገደሉት ሰዎች መካከል ሁለቱ የሴኔጋል ዜጎች ነበሩ። በዚህም የተነሳ በጎሬቤት ሀገር ሴኔጋል የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል።በተጨማሪም የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋምቢያ ላይ ማዕቀብ እንደሚጥል ዝቷል። እንዲሁም ፕሬዚዳንት ጃሜም አለም አቀፉን ደረጃ እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል። ጥሩው ነገር የጋምቢያ መንግስት ለመስከረም አጋማሽ የሞት ፍርድ የበየነባቸውን 38 ሰዎች እስካሁን አልረሸነም። የሞቱ ቅጣት ለጊዜው መቆሙን የፕሬዚደንታዊው ጽህፈት ቤት አስታወቋል። ማኔ ይህንን ውሳኔ በቀና ቢቀበሉም ስጋት አላቸው።

«ይህ ጥሩ ዜና ነው። ይህ መንግስት »ሞራቶሪውም» ሲል ይጠራዋል። ያም ማለት አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት ጊዜ የሞቱን ቅጣት እንደገና ስራ ላይ ሊውል ይችላል። ያህያ ጃሜን እና ባለፉት አመታት የሰሯቸውን ተግባራት የሚያውቅ ሁሉ ለሰው ህይወት ከበሬታ እንደሌላቸው ያውቃል። አንድ ቀን ተነስተው የግድያውን ቅጣት እንደገና ጀምሬያለሁ ሊሉ ይችላል።»

የአውሮፓ ህብረት የሞቱ ቅጣትለጊዜው ቆሞዋል የተባለበትን ውሳኔ ተከተሎ በርግጥ የዛተውን ማዕቀብ መጣሉ ገና በውል አልታወቀም። ዓለም አቀፍ የሞት ቅጣት ውግዘት ቀን ዛሬ ታስቦ በዋለበት ቀን የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪቃ ጠበብት የሞቱን ቅጣት ማስቀረት ስለሚቻልበት ጉዳይ ለሚመለከተው የአውሮፓ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ሀሳብ ያቀርባሉ። ምክር ቤቱ ውሳኔ እስኪደርስ ግን ብዙ ጊዜ መውሰዱ አይቀርም።

ኤሪክ ሴጉንዳ

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic