ዓለም አቀፍ የደህንነት ጉባኤ በጀርመን ሙኒክ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.02.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ዓለም አቀፍ የደህንነት ጉባኤ በጀርመን ሙኒክ

ዛሬ ቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ተወግዶ በምትኩ ምዕራቡ ዓለም በዋናነት ከኢራንና ሰሜን ኮሪያ ስጋት በተጨማሪ፤ አልቃይዳን ከበስተ አፍጋኒስታን እያስተናገደ ይገኛል። ታዲያ ዓለም ካዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ለህመሙ ማስታገሻ መድሀኒት ባፋጣኝ ይሻል፤ ግልፅና ሁሉን ያሳተፈ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ።

ኢራን፣ አሜሪካ፣ አፍጋኒስታን

ኢራን፣ አሜሪካ፣ አፍጋኒስታን

አዲሱ የUS አሜሪካ አስተዳደር፤ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን አስመልክቶ ያዘጋጀውን ዕቅድ የመጀመሪያ ማብራሪያ በጀርመን ሙኒክ ዓመታዊ የደህንነት ጉባኤ ላይ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። አርባ አምስተኛው ዓመታዊ የደህንነት ጉባኤ ዛሬ ከምሽቱ አንድ ሠአት ላይ በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሽታይንማየር ንግግር ተከፍቶ እስከ ፊታችን እሁድ ይዘልቃል። ኢራን፣ አፍጋኒስታን፣ አቶሚክ ሀይልና ሞስኮ ዋና የመነጋገሪያ አጀንዳ ይሆናሉ።