ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እና ወጣቱ | ባህል | DW | 21.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እና ወጣቱ

በዓለማችን አብዛኞቹ ክፍሎች በነሐሴ ወር የሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ኢትዮጵያ ውስጥም ተከብሩዋል። ይህ የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ርዕስ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጎርጎሮሳዊውን ነሐሴ 12 ቀን የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በማለት ሰይሟል። አላማው ወጣቱን ይበልጥ በማህበረሰቡ ዘንድ ማሳተፍ እና ተሰሚነት እንዲያገኝ ማድረግ ነው።በርካታ ሀገራት በሚያስቡት በዚህ ዓመታዊ ቀን፤ ወጣቶች ለዓለም የሚያበረክቱትን አስተዋፅዎ፣ የሚያስተዋውቁ፣ ጉባኤዎች ይካሄዳሉ። የስፖርት እና የባህል አውደ ርዕዮች ይዘጋጃሉ። ቀኑ ዘንድሮም ኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳዩ በሚመለከታቸው የተለያዩ አካላት ታስቧል።

Symbolbild Internationaler Friedenstag der UN

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወጣት የሚላቸው እድሜያቸው ከ 15- 24 ክልል ውስጥ የሚገኙትን ነው። ከነዚህም አብዛኞቹ ወጣቶች የሚኖሩት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አዳጊ ሀገራት ነው። የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የሚለው ሀሳብ የተፀነሰው እኢአ በ1991 ዓም አውስትሪያ- ቪዬና ውስጥ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የአለም የወጣቶች መድረክ ላይ በተሳተፉ ወጣቶች ነበር።የዘንድሮውን የዓለም የወጣቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሀፊ ባን ኪ ሙን « የወጣቱ ተሳትፎ ከመጪውም በላይ ትልቅ ዋጋ አለው» የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። ወጣቱ ይህን ያህል ሚና የሚጫወት ከሆነ ደግሞ ፤ ፍላጎቱን የመግለፅ፣ የመሳተፉ ፣ የመወሰን መብት ሊከበርለት ይገባል። ከማህበረሰቡ 40 ከመቶ በላይ ወጣት በሆነበትስ ኢትዮጵያ ወጣቱ ምን ያህል ተደማጭነት አለው? ጥቂት ወጣቶችን አነጋግረናል።

በኢትዮጵያ ሴቶች፣ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አብይ ኤፍሬም፤ ዘንድሮ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በኢትዮጵያ እንዴት እንደተከበረ ገልፆልናል። ዘገባውን በድምፅ ያገኛሉ።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic