ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን
ሰኞ፣ ሰኔ 13 2014ማስታወቂያ
የዓለም የስደተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታሰብበት በዛሬው ዕለት ፈረንሳይ ውስጥ ደግሞ የስደተኞች የምግብ ዝግጅት በአል በሚል በልዩ ዝግጅት እየተከበረ ነው። በአሉ በስደተኛ ምግብ አብሳዮች እና በአካባቢው የምግብ ቤቶች መካከል ትብብርን ለመፍጠር በበጎ ፈቃደኛ ዜጎች ተነሳሽነት ከጎርጎሪዮሳዊው 2016 ዓም ጀምሮ በየዓመቱ የሚካሄድ ነው። በዚህ ዝግጅት ላይ የሚካፈሉ ኑሯቸውን በፈረንሳይ ያደረጉ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ስደተኞችን ጨምሮ ምግብ ማብሰል ፍላጎት ያላቸው እና በሙያው ለመሰማራት ለሚፈልጉ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ነገሮችን ለማመቻቸት ብሎም ከማኅበረሰቡ ጋር በቀላሉ ለመዋሃድ እንዲችሉ ይኽ በአል አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ