ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር-ኢትዮጵያና የአስቸኳይ ርዳታ ጥሪ | ኢትዮጵያ | DW | 26.08.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር-ኢትዮጵያና የአስቸኳይ ርዳታ ጥሪ

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር እና የቀይ ጨረቃ ድርጅት በደቡብ ኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ሰበብ ለተጎዳው ህዝብ መርጃ የሚሆን ተጨማሪ አምስት ሚልዮን ዩሮ እንዲቀርብ ጥሪ አቀረበ።

ድርቅ ያጠቃው አርብቶ አደር

ድርቅ ያጠቃው አርብቶ አደር

በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር የድርቅ መርጃ ተግባር ኃላፊ ሎሬንሶ ቪዮላንቴ እንዳስታወቁት፡ ሁኔታዎች ባለፉት ሁለት ወራት ይበልጡን አሳሳቢ እየሆነ መጥተው ህዝቡ ራሱን መመገብ የማይችልበት ደረጃ ደርሶዋል።