1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን በጀርመን

ሰኞ፣ ሚያዝያ 23 2009

የዓለም ሠራተኞች ቀን በተለያዩ ሃገራት በአደባባይ ሠልፎች ታጅቦ ሲከበር ውሏል። ጀርመን በተለይ በርሊን ከተማ ውስጥ ከአምስት ሺህ በላይ ፖሊሶች እና የጥበቃ ሠራተኞች በተሰማሩበት ነው ቀኑ ተከብሮ የዋለው። በጥንካሬው የሚታወቀው የጀርመን የሠራተኞች ማኅበር (DGB) ሠራተኞች የተሻለ ደሞዝ እና የሥራ ኹኔታ እንዲፈጠርላቸው ጥሪ አስተላልፏል።

https://p.dw.com/p/2cC6n
Tag der Arbeit Deutschland Maikundgebung in Berlin DGB Chef Hoffmann
ምስል Getty Images/C. Koall

Q&A Berlin (World workers day)* - MP3-Stereo

የዓለም ሠራተኞች ቀን በተለያዩ ሃገራት በአደባባይ ሠልፎች ታጅቦ ሲከበር ውሏል። ጀርመን በተለይ በርሊን ከተማ ውስጥ ከአምስት ሺህ በላይ ፖሊሶች እና የጥበቃ ሠራተኞች በተሰማሩበት ነው ቀኑ ተከብሮ የዋለው። በጥንካሬው የሚታወቀው የጀርመን የሠራተኞች ማኅበር (DGB) ሠራተኞች የተሻለ ደሞዝ እና የሥራ ኹኔታ እንዲፈጠርላቸው ጥሪ አስተላልፏል። በጀርመን ሰባት ሚሊዮን ሠራተኞች በዝቅተኛ ደሞዝ እንደሚሠሩም ማኅበሩ (DGB) ተናግሯል። 

ከጀርመን ውጪ ባሉ ከተሞች ደግሞ፦ የሩስያ መዲና ሞስኮ ውስጥ 130,000 ግድም ሠልፈኞች በቀዩ አደባባይ ታይተዋል። በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ውስጥ የሠራተኞችን ቀን የሚያከብሩ ሰልፈኞችን ለማወክ የሞከሩ ሌሎች ሰልፈኞችን ፖሊስ በአስለቃሽ ጢስ መበተኑ ታውቋል። ሰልፈኞች የፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፖለቲከኛዋ ማሪን ለፔን በመጪው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምጽ እንዳያገኙ ጥሪ ሲያስተላልፉ ተሰምተዋል።

በስፔን ሁለቱ ታላላቅ የሠራተኛ ማኅበራት በ70 ከተሞች ሰልፍ ጠርተዋል። ወግ አጥባቂው የስፔን መንግሥት የሠራተኛ መዋቅሩን በመቀየር ደሞዝ እና ጡረታ እንዲሻሻል ጠይቀዋል። በሐቫና  ኩባ ደግሞ አንድ የዩናይትድ ስቴትስን ሠንደቅ ዓላማ ያውለበልብ የነበረ ግለሰብ ከሰልፈኞቹ እየተገፈተረ ከመውጣቱ በስተቀር የአደባባይ ሰልፉ ያለምንም እንከን መከናወኑ ተሰምቷል። በሌሎች ታላላቅ ከተሞችም ሰልፎች ተከናውነዋል። ጀርመን መዲና በርሊን ውስጥ የፀጥታ ጥበቃው ከምን ጊዜው በላይ መጠናከሩ ተገልጧል።

ይልማ ኃይለሚካኤል 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ