ዓለም በጎርጎሪዮሳዊዉ 2015 ዓ.ም. | ዓለም | DW | 03.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ዓለም በጎርጎሪዮሳዊዉ 2015 ዓ.ም.

ጎርጎሪዮሳዊዉ 2015 ዓ.ም. ዛሬ አምና ሆኗል። ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት በአፍሪቃ እና በሌላዉም የዓለም ክፍል በአንዳንድ ሃገራት ሰላማዊ ምርጫዎች እና የስልጣን ሽግግሮች ታይተዋል። በተቃራኒዉም ሕገ መንግሥቶቻቸዉን በመተላለፍ የመሪዎች በስልጣን የመቆየት ፅኑ ፍላጎት ብጥብጥ ያስከተለባቸዉ ሃገራትም ነበሩ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 26:53

ጎርጎሪዮሳዊዉ 2015 ዓ.ም.

2015 ዓ.ም. በርካቶች ከመኖሪያ ቀያቸዉ የተሰደዱበትም ነበር። በዚህ ምክንያትም በተለይ አዉሮጳ በስደተኛ ብዛት ስትማረር ዓመቱን ፈጽማለች፤ አሁንም መፍትሄ ባታገኝለትም። ከዚም ሌላ በዚሁ ዓመት በሩሲያ እና በምዕራባዉያን ሃገራት መካከል የተቀሰቀሰዉ ፍeጥጫ ቀዝቃዛዉን ጦርነት ዳግም የሚያመጣ መስሎ የታየበት፤ ለረዥም ዓመታት ተፋጥጠዉ የቆዩት ኩባ እና ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ሻካራ ግንኙነታቸዉን ያለሰለሱበትም ነበር። ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በየደረጃዉ ከተካሄዱ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች አንዱ ከሆነዉ የአየር ንብረት ተመልካች ጉባኤም፤ ከባቢ አየርን የሚበክሉ ጋዞች ስለመቀነስም አዎንታዊ ነገር የተሰማዉ በ2015ዓ,ም ነበር። በየተወሰኑ ዓመታት እያደባ የሚከሰተዉ ኤሊኒኞ የተሰኘዉ የአየር ጠባይ ለዉጥ ክስተትም በተለያዩ ሃገራት ድርቅ፣ ከፍተኛ ሙቀት፣ የዝናብ እጥረት፣ ዶፍ ዝናብና ጎርፍም ያስከተለበት ዓመት ነበር። ዶቼ ቬለ በዚህ ሳምንት ባካሄደዉ ዓመቱን የቃኘ ዉይይት በርካታ ነጥቦች ተነስተዋል። ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic