ዓለማቀፉ የመጸዳጃ ቤት ቀን እና ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 19.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዓለማቀፉ የመጸዳጃ ቤት ቀን እና ኢትዮጵያ

የዓለም የመጸዳጃ ቤት ቀን በመላዉ ዓለም ዛሬ ታስቦ ዋለ። በኢትዮጵያ ባለፉት አስር ዓመታት የመጸዳጃ ቤት እና አጠቃቀሙን በተመለከተ ትልቅ መሻሻል ቢታይም አሁንም በርካታ ነዋሪዎች መጸዳጃ ቤት እንደሌላቸዉና፤ በየቦታዉ እንደሚጸዳዱ ተጠቅሶአል።

እንዲያም ሆኖ ኢትዮጵያ እስከ መጭዉ የጎርጎረሳዊ 2018 ዓ,ም ድረስ ዜጎች መጸዳጃ ቤት እንዲኖራቸዉ ጥረት ለማደግ መዘጋጀቷ ተነግሯል።

(Achtung Redaktionen: Sperrfrist 15. November 23.00 Uhr) ARCHIV - Ein Schild mit der Aufschrift «WC» und einem Hinweispfeil hängt an einem Haus in Landshut (Niederbayern), aufgenommen am 23.03.2008. Bei nur der Hälfte der Weltbevölkerung kommt das Wasser aus einem Wasserhahn im Haus. Rund 20 Prozent haben nicht einmal ein Plumpsklo. Das berichtet eine internationale Forschergruppe anlässlich des Welttoilettentages am 19. November. Foto: Armin Weigel (zu dpa 0344 vom 15.11.2010) +++(c) dpa - Bildfunk+++

ዛሬ በተለያዩ የዓለም ሃገራት ታስቦ የዋለዉ የዓለም የመፀዳጃ ቤት ቀን በኢትዮጵያ በኦሮምያ ክልል አዳማ ከተማ በሚገኘዉ አበበ ቢቂላ ስቴድዮምም በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቧል። በዚህ ዝግጅት ላይ ሳሉ በስልክ ያገኘናቸዉ በኢትዮጵያ በተመ የሕፃናት መርጃ ድርጅት UNICEF የዉሃ እና የግል ንፅሕና መርሃግብር ባለሞያ አቶ ሙጬ ኪዳኑ፤ እንደሚሉት ቀኑን በደማቅ ታስቦ መዋሉ እንዳለ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓትም ወደ 38 ሚሊዮን ህዝብ የመፀዳጃ ቤት ተጠቃሚ አይደለም

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የተመ የሕፃናት መርጃ ድርጅት UNICEF የግል ንፅህናን የሚመለከተዉ መርሃግብር ተጠሪ ሳሙኤል ጎድፍሪ እንደሚሉት ዛሬ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተከበረዉ የመጸዳጃ ቤት ቀን፤ በተለይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በንፅሕና አጠባበቅ ረገድ ትልቅ መሻሻል መታየቱን የምንገልፅበት ቀን ነዉ፤

«በተለይ ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ከሚገኙ ሃገራት የጽዳት፤ እና የግል ንፅህናን በተመለከተ መሻሻል የታየባት ሀገር ናት፤ በመቀጠል መንግሥት እስከ መጭዉ የጎርጎረሳዉያን 2018 ዓ,ም እያንዳንዱ ነዋሪ የግል ንጽህናን ለመጠበቅ የሚያስችል እቅድ ነድፏል፤ ዩኒሴፍ በዚህ ሳምንት የሚከበረዉን የግል ንፅህና አጠባበቅ በተመለከተ በዘርፉ የሚሰሩትን የተለያዩ ተቋማትን በአንድ አሰባስቦአል።»

በዩኒሴፍ የግል ንፅህና መርሃግብር ዋና ተጠሪ፤ ሳሙኤል ጎድፍሪ፤ በንፅህና አጠባበቅ ረገድ በሚሰጠዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ከባዱ ልማድን ማስለወጡ ነዉ፤

Teilnehmer nehmen am Mittwoch, 19. November 2008, dem World Toilet Day, vor dem Hauptbahnhof in Berlin auf einigen der 50 aufgestellten Toiletten an einer Pressekonferenz teil. Das Jahr 2008 wurde von den Vereinten Nationen zum Internationalen Jahr der sanitaeren Grundversorgung ausgerufen. (AP Photo/Franka Bruns) ---Participants attend a press conference during World Toilet Day in front of the main train station in Berlin, Wednesday, Nov. 19, 2008. The United Nation announced 2008 to the International Year of Sanitation. (AP Photo/Franka Bruns)

« ንፅህናን ለመጠበቅ በሚከናወነዉ እንቅስቃሴ ፤ ከባዱ ፈተና ይህ በሚመለከት የማህበረሰቡን ልማድ ማስለወጡ ሥራ ነዉ። ስለዚህ ይህን ለማሳካት አዲስ አካሄድ ተግባራዊ ለማድረግ በኢትዮጵያ ዉስጥ እየተሞከረ ነዉ፤ ይህም ኅብረተሰቡ ስለ ግል ንፅህና እና ጤና አጠባበቅ ዘዴ ይነጋገር የሚል ሲሆን፤ ይህም የታቀደዉን ግብ ለመምታት እንደሚረዳ ይታሰባል።» በ UNICEF የንጹህ ዉሃ እና የግል ንፅህና መርሃግብር ባለሞያ አቶ ሙጬ ኪዳኑ፤ እንደሚሉት ደግሞ ኢትዮጵያ እስከ 2018 ዓ,ም የግል ንፅህና አጠባበቅን ለማማላት የያዘችዉ መረሃ-ግብር ለእያንዳንዱ የመፀዳጃ ቤት የሚቆም ሳይሆን የንፅህና አጠባበቅን እና የመፀዳጃ ቤት ጥቅምን ለመላዉ ነዋሪ የግንዛቤ መስጠት ነዉ።

አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ

Audios and videos on the topic