ውጥረት በሰንደቅ ዓላማ እና ዓርማ ሰበብ | ኢትዮጵያ | DW | 14.09.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ውጥረት በሰንደቅ ዓላማ እና ዓርማ ሰበብ

በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱትን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራር አባላት ለመቀበል  ደጋፊዎች በያዙት ዝግጅት ወቅት በሰንደቅ ዓላማ ሰበብ ትናንት ከአስኮ መድሀኒዓለም እስከ አውቶቡስ ተራ፣ ዛሬ ደግሞ በሰሜን ማዘጋጃ እና ቤቴል በተፈጠሩ ግጭቶች ሰዎች መጎዳታቸው እና መኪኖችም መሰበራቸው ተሰምቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:09

ውጥረት በሰንደቅ ዓላማ እና ዓርማ ሰበብ

የአዲስ አበባ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር እንደዘገበው፣ ግጭቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት በሀገሪቱ እየሰፈነ ያለው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ባንዲራንም ስለሚያጠቃልል የሌላኛውን አስተሳሰብ መግፋት አይገባም  ፣ መንግሥትም  ግጭቱን ለማርገብ ርምጃ ይወስዳል ብለዋል። 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic