ውጤት ያላስገኘው የደቡብ ሱዳን ውይይት | አፍሪቃ | DW | 24.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ውጤት ያላስገኘው የደቡብ ሱዳን ውይይት

በጎርጎሪዮሳዊው 2015 ዓም የከሸፈውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት እንደገና ለማነቃቃት በአዲስ አበባ ስብሰባ ትናንት ሌሊት ካላንዳች ስምምነት ተጠናቀቀ። ለአስር ቀናት የዘለቀው ስብሰባው በዋነኛነት በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል የሚታየውን ልዩነት የማጥበብ ዓላማ ይዞ የተነሳ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:12

መፍትሔ ያልተገኘለት የደቡብ ሱዳን ውዝግብ

የአደራዳሪነቱን ሚና የያዘው የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት እንደገለጸው፣ ተቀናቃኞቹ ወገኖች በስልጣን መጋራቱ እና በፀጥታ ጥበቃ ጉዳዮች ላይ አስማሚ ሀሳብ ላይ በመድረስ የርስ በርሱን ጦርነት እንዲያበቁ ቀናት በተጠናከረ ሁኔታ ያደረገው ጥረት ፍሬ ሳያስገኝ ቀርቷል። በድርድሩ የተገኙት የኖርዌይ፣ የዩኤስ አሜሪካ እና የብሪታንያ ተወካዮች ኢጋድ ተቀናቃኖቹን ወገኖች ለማግባባት የጀመረውን ጥረት እንዲገፋበት ጠይቀዋል። በርስበርሱ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን የተገደሉ ሲሆን፣ ሚልዮኖችም ተፈናቅለዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic