ውይይት፥ ወቅታዊዉ የኢትዮጵያ ሁኔታ ወዴት እያመራ ነዉ? | ኢትዮጵያ | DW | 15.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ውይይት፥ ወቅታዊዉ የኢትዮጵያ ሁኔታ ወዴት እያመራ ነዉ?

ኢትዮጵያ ዉስጥ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ እየበረደ ዳግም የሚያንሰራራዉ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በዚህ ሳምንትም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል። በዚህ ወቅትም ሰዎች ሞተዋል፤ ቆስለዋልም። በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የድንበር አካባቢዎች ለሰዎች ሕይወት መጥፋትና ለበርካቶች መፈናቀል ምክንያት የሆነዉ ግጭትም እልባት አላገኘም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:02
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
30:02 ደቂቃ

ወቅታዊዉ የኢትዮጵያ ሁኔታ

ተመሳሳይ የድንበር ዉዝግብ በተነሳባቸዉ በአፋር እና አማራ፤ በቡርጂ እና ጉጂም ግጭቱ ያለዘላቂ መፍትሄ ተዳፍኗል። ግጭቶቹ ተባብሰዉ ወደከፋ ደረጃ ሳይደርሱ ሊከላከላቸዉ ይገባ ነበር በሚል ማዕከላዊዉ መንግሥት በሚተችበት በዚህ ወቅትም የሀገሪቱ ምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ስልጣን ለመልቀቅ ጠይቀዋል። እዚህም እዚያም የሚነሱ ግጭቶች እና መፈናቀሎችን የሚመለከቱ ሀገሪቱ ወዴት እየሄደች ነዉ በሚል ስጋታቸዉን ይገልጻሉ። በአንፃሩ ኢትዮጵያዉያን አብሮ የመኖርን ጥቅም ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ ያወቁበት ወቅት በመሆኑ አያሰጋም የሚሉም አልጠፉም። በእርግጥ የሀገሪቱ የፖለቲካ አቅጣጫ ወዴት እያመራ ነዉ?  የመወያያ ርዕሳችን ነዉ። ሙሉ ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች