ውይይት ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ | ኢትዮጵያ | DW | 03.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ውይይት ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ

የቀድሞው የደርግ ስርዓት ከተወገደ ከ25 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ በዘፈቀደ ማሰር እና በመደዳ መግደል ሃሳብን በነፃ መግለጽ እና የመሰብሰብ ነፃነት መገደብ መቀጠሉ ተገልጿል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:05

ውይይት ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ

«መንግሥት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን እንዲያቆም እጠይቃለሁ ። በተለይም በጋምቤላ በኦጋዴን በኦሮምያ ህዝቡ እየተሰቃየ ነው ። ንጹሃን ሰዎች ንጹሃን ኦሮሞዎች የጋምቤላ ህዝቦች ኦጋዴኖች አማራዎች እየተሰቃዩ ነው ። ስለዚህ በኢትዮጵያ ግድያ ይቁም ! መሬት መቀራመት ይቁም ሰዎችን ማፈናቀል ይቁም »
ስለኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ትናንት ናይሮቢ ውስጥ የተካሄደ ውይይት ተሳታፊ የተናገሩት ነው ።በዚሁ ውይይት ላይ ባለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሰ መሄዱ ተገለጿል ። በሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪቃ የአፍሪቃ ቀንድ እና የታላላቅ ኃይቆች አካባቢ አገራት ቅርንጫፍ ቢሮ አዘጋጅነት የተካሄደው ውይይት የቀድሞው የደርግ ስርዓት ከተወገደ ከ25 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ በዘፈቀደ ማሰር እና በመደዳ መግደል ሃሳብን በነፃ መግለጽ እና የመሰብሰብ ነፃነት መገደብ መቀጠሉ ተገልጿል ። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ዓለም ዓቀፍ ትኩረት እንዲሰጠውም ተጠይቋል ። ውይይቱን የተከታተለውን የናይሮቢው ወኪላችንን በስልክ አነጋግረነዋል።

ፋሲል ግርማ


ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic