ውይይት፦ ምርጫ፣ የጊዜ እጥረትና የዝግጅቱ ብዛት | ኢትዮጵያ | DW | 18.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ውይይት፦ ምርጫ፣ የጊዜ እጥረትና የዝግጅቱ ብዛት

ተፎካካሪዎች፣ አስመራጭና ተመራጮች በዚሕ አጭር ጊዜ ዉስጥ ተወያይተዉ፣ ተስማምተዉ፣ አወዳድረዉ፤ ወይም ተወዳድረዉ፣ ሐገር አረጋግተዉ፣ ሕዝብ ቆጥረዉ ነፃና ትክክለኛ ምርጫ ማድረግና መምራት መቻላቸዉ እያጠያየቀ ነዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:03

ሁለት ሐሳብ ሁለት ፖለቲከኞች «የምርጫዉ የጊዜ ሠሌዳ መራዘም አለበት»፣ «ጊዜዉ እንዲራዘም ሕዝበ ዉሳኔ ይጠራ»

እስካሁን በተያዘዉ ዕቅድ መሠረት ኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የምታስተናግድበት ጊዜ ከዓመት በላይ ብዙም አልቀረዉም።የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮችና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለሥልጣናት ግን የቦርዱን ኃላፊነት፣ አሠራር፣ አወቃቀር፣ደንብንና ምናልባትም መሪዎቹን ለማሻሻልና ለመቀየር ገና እየተወያዩ ነዉ።የብዙ አካባቢ ፀጥታም አስተማማኝ አይደለም።በዚያ ላይ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ የስታትስቲክስ መስሪያ ቤት የሐገሪቱን ሕዝብ ለመቁጠር ገና እየተዘጋጀ ነዉ።በዚሕም ምክንያት የመራጩን ሕዝብ ትክክለኛ ቁጥር በዉል መናገር አይቻልም።እስካሁን ባለን መረጃ ግን ከ36 እስከ 40 ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ  ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይገመታል።ተፎካካሪዎች፣ አስመራጭና ተመራጮች በዚሕ አጭር ጊዜ ዉስጥ ተወያይተዉ፣ ተስማምተዉ፣ አወዳድረዉ፤ ወይም ተወዳድረዉ፣ ሐገር አረጋግተዉ፣ ሕዝብ ቆጥረዉ ነፃና ትክክለኛ ምርጫ ማድረግና መምራት መቻላቸዉ እያጠያየቀ ነዉ።አጠያያቂዉ ጉዳይ የዉይይታችን ትኩረት ነዉ።ሰወስት እንግዶች አሉን።

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች