ውዝግብ በኢትዮ ኦ ተ ቤተክርስቲያን | ኢትዮጵያ | DW | 31.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ውዝግብ በኢትዮ ኦ ተ ቤተክርስቲያን

አቡነ ጳውሎስ በህይወት ሳሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቀ ሰላም ውይይት ቢቀጥልም ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ግልፅ አልተደረገም። ሰሞኑን ለሽምግልና ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ከሄዱ ሁለት አባቶች አንዱ ከሃገር ተገደው ወደመጡበት መመለሳቸው ሌላኛው ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ ዘገባዎች ወጥተዋል።

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Sitz des Patriarchen der äthiopisch-orthodoxen Kirche in Addis Abeba Thema: Alle vier großen Religionsgemeinschaften Äthiopiens - Orthodoxe und katholische Christen, Protestanten und Muslime - haben im Vorfeld der Wahl in einem gemeinsamen Appell für einen friedlichen Wahlgang geworben. Die beiden Tauben vor dem Sitz des Abuna, des Patriarchen der Orthodoxie Äthiopiens, stehen dafür sinnbildlich. Schlagwörter: Orthodoxie Äthiopien, Abuna Paulos, Dialog der Religionen, Wahl Äthiopien 2010, Elections Ethiopia 2010የቀድሞው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ጳውሎስ ካረፉበት ጊዜ አንስቶ የአዲስ ፓትሪያርክ ምርጫ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ እንዳወዛገበ ነው። በሌላ በኩል አቡነ ጳውሎስ በህይወት ሳሉ አንስቶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቀ ሰላም ውይይት ቢቀጥልም ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ግልፅ አልተደረገም። በዚህ ሁኔታ ደግሞ ሰሞኑን ለሽምግልና ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ከሄዱ ሁለት አባቶች አንዱ ከሃገር ተገደው ወደመጡበት መመለሳቸው ሌላኛው ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ አንዳንድ ዘገባዎች ወጥተዋል። በነዚህ ጉዳዮች ላይ የአዲስ አበባውን ዘገቢያችንን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን አነጋግራናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic