ውሳኔ የሚጠብቀው የኬንያ ምርጫ ውጤት | አፍሪቃ | DW | 28.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ውሳኔ የሚጠብቀው የኬንያ ምርጫ ውጤት

ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ውድቅ እንዲሆን የጠየቁበትን ምክንያት የሚያስረዳ ወደ 40 ገፅ በሚጠጋ ሰነድ በሂደት የተከሰቱ ማጭበርበሮችን የዘረዘረ ማመልከቻ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል ። በማመልከቻቸው የምርጫ ኮሚሽን ፣ የድምፅ አሰጣጡ ስርዓት እንዲቀየር መፍቀዱ ራሱ ህገ ወጥ ነው ሲሉ ተቃውመዋል ።

default

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንትናና ዛሬ የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ኡሁሩ ኬንያታ የካቲት 25 ፣ 2005 የተካሄደው  የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ  አሸናፊ ናቸው ሲል ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሽር የቀረቡለትን መከራከራያዎች ሲያደምጥ ውሏል ። መከራከሪያዎቹን ያቀረቡት  የኬንያ የሲቪል ማህበርና በምርጫው ተሸናፊ መባላቸውን ያልተቀበሉት የጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ የህግ አማካሪዎች ናቸው ። በህጉ መሠረት ፍርድ ቤቱ እስከ መጨረሻው ቀነ ገደብ  ቅዳሜ ድረስ ውሳኔ ማሳለፍ ይጠበቅበታል ። 

በአዲሱ የኬንያ ህገ መንግሥት መሠረት ማንኛውም ኬንያዊ የምርጫ ውጤት በተገለጠ በ7 ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን ለፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል  ። በርካታ ኬንያውያውን ይህን እድል ወዲያውኑ ተጠቅመውበታል ።ከነዚህም መካከል በፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ተሸናፊ የተባሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ይገኙበታል ። የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት ራይላ ኦዲንጋ ፣ከተቀናቃኛቸው ኡሁሩ ኬንያታ በ7 በመቶ ያነሰ ድምፅ ነው ያገኙት ።

Kenia Premierminister Raila Odinga Wahl Präsidentschaftswahll Nairobi Anzweiflung Anhänger Protest

ራይላ ኦዲንጋና ደጋፊዎቻቸው

የተሃድሶና የዲሞክራሲ ጥምረት የተሰኘው የኦዲንጋ ፓርቲ የምርጫው ውጤት ሆን ተብሎ እንደተጭበረበረ ይሰማዋል ። ፓርቲው እጎአ በ2007 አ.ም ተደርጎ የነበርውን ምርጫ ውጤት በመቃወም መከራከሩ የሚታወስ ነው ። የኦዲንጋ ፓርቲና የተጣማሪዎቻቸው የምርጫ ጉዳይ ጠበቃ አሞስ ዋኮ ፓርቲው አሁንም ተመሳሳዩ ስህተት እንዲደገም እንደማያደርግ ናይሮቢ ውስጥ ለተሰበሰበ ህዝብ  ተናግረዋል ። «እ.ጎ.አ የ2007 ቱ ምርጫ ውጤት የተሳሳተ እንደነበር እናውቃለን ። አሁን ደግሞ የተሰጡን ድምጾች እንደገና እንዲወሰዱብን አናደርግም ።  »

በዚህ መነሻነት  ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ውድቅ እንዲሆን የጠየቁበትን ምክንያት የሚያስረዳ ወደ 40  ገፅ በሚጠጋ ሰነድ በሂደት የተከሰቱ ማጭበርበሮችን  የዘረዘረ ማመልከቻ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል ። በማመልከቻቸው የምርጫ ኮሚሽን ፣ የድምፅ አሰጣጡ ስርዓት እንዲቀየር መፍቀዱ ራሱ ህገ ወጥ ነው ሲሉ ተቃውመዋል ። የምርጫው ውጤት መሰረዝ ለኦዲንጋ ብቸኛው ተስፋ አይደለም ።

Kenia Premierminister Raila Odinga Wahl Präsidentschaftswahll Nairobi Anzweiflung Anhänger Protest

ተቃውሞ በናይሮቢ

የምርጫ ኮሚሽኑ አሸናፊነታቸውን በይፋ ያረጋገጠላቸው ኡሁሩ ኬንያታን ለማንሳት በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ዳግም የድምፅ ቆጠራ መካሄድ ብቻ በቂ ሊሆን ይችላል ።  የኬንያ የፖለቲካ ጉዳዮች ተከታታይ ማቻርያ ሙዌኔ  በድጋሚ ድምፅ ከተቆጠረ ውጤቱ ሊቀየር ይቻላል ይላሉ ።  «ዳግም ቆጠራ ተካሂዶ ኡሁሩ ኬንያታ ለርሳቸው ያልተሰጠ 8 ሺህ ድምፅ ማግኘታቸው ከተደረሰበት የተሰጣቸው ድምፅ ከ 50 በመቶ ያንሳል ። ምናልባትም ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ ዙር ምርጫ እንዲካሄድ ሊወስን ይችላል ። »

ይህ ከሆነ ደግሞ ራይላ ኦዲንጋ ተጨባጭ የማሸነፍ እድል ይኖራቸዋል ። በመለያው ዙር ምርጫ ራይላ ኦዲንጋ ፣ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ ለሌሎች እጩዎች የተሰጠባቸውን ድምፅ ሊያገኙ ይችላሉ ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት  ባለፈው ሰኞ  ከ291 ዱ የምርጫ ጣቢያዎች በ22 ቱ በድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ መወሰኑ ለኦዲንጋ የመጀመሪያው ስኬት ነበር ። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ሌላ ለቀረቡለት ሌሎች አቤቱታዎችም ውሳኔ ይሰጣል ። በአፍሪቃ ለግልፅ አስተዳደር  የሚንቀሳቀሰው መንግሥታዊ ያልሆነው  በእንግሊዘኛው ምህፃር AFRICOG በመባል የሚጠራው ማዕከልም የምርጫው ውጤት እንዲሰረዝ ጠይቋል ።

Kenyatta Sieger der Präsidentenwahl in Kenia

አሸናፊው ኡሁሩ ኬንያታ

፤ በዚህ ምክንያት ለኬንያታ የተሰጠው ድምፅ ከፍ ብሏል ሲል ይከራከራል ። 6ቱ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞች የቀረቡላቸውን አቤቱታዎች በሙሉ መርመረው  እንዲወስኑ በህገ መንግሥቱ የተቀመጠው የ2 ሳምንት ጊዜ  ሳያንሳቸው አይቀርም ። ዳኞቹ  የመራጮች ምዝገባ  እንዲመረመር AFRICOG ማክሰኞ ያቀረበውን ማመልከቻ አልተቀበሉም ።  ዳኛ ሞሐመድ ኢብራሂም ምክንያቱን አስረድተዋል ።

«አቤቱታ አቅራቢዎቹ ማመልከቻቸውን ፍርድ ቤት ጉዳዩን መስማት ከመጀመሩ በፊት በተገቢው ጊዜ አቅርበው ቢሆን ኖሮ  በአመዛኙ ሊታይ ይችል ነበር ። ሆኖም አሁን ባለው  ሁኔታ ፍርድ ቤቱ ማመልከቻቸውን አይቀበልም ። »

የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን እንደሚለው የመራጮች ምዝገባዎችን ለማጣራት ከ 7 እስከ 10 ቀናት ይወስዳል ። በሃገሪቱ በመላ የሚገኙት የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ቁጥር 33,400 ይጠጋል ። ምርመራው

ፊሊፕ ሳንድነር 

 ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic