ዉጥረት የተከተለዉ የኬንያ ምርጫ | አፍሪቃ | DW | 10.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ዉጥረት የተከተለዉ የኬንያ ምርጫ

ማክሰኞ ዕለት ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያካሄደችዉ ኬንያ በ24 ሰዓት ዉስጥ ዉጤት ይፋ ይሆናል ተብሎ ቢጠበቅም ዛሬ ከቀትር በኋላ እንደሚዘገይ ተገልጿል። የምርጫ ኮሚሽኑ እንደሚለዉ እስካሁን ስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታ እየመሩ ነዉ። ተፎካካሪያቸዉ የተቃዉሞ ፖለቲካ መሪዉ ራይላ ኦዲንጋ ግን ደጋፊዎቻቸዉ ይህን እንዳይቀበሉ አሳስበዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:57
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:57 ደቂቃ

ሕዝቡ ውጤቱን በንቃት እየተጠባበቀ ነው።

 ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች የምርጫዉን አያያዝ ማድነቃቸዉ ቢነገርም በናይሮቢና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ሕዝቡ ከወዲሁ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ መጀመሩን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ፖሊስም በአስለቃሽ ጋዝ ጎዳና የወጡት ለመበተን መሞከሩም ተገልጿል። የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን የምርጫዉን የኢንተርኔት መረጃ ለመስበር ተሞክሮ መክሸፉን አስታዉቋል። ከዓመታት በፊት በምርጫ ዉዝግብ ምክንያት የደረሰዉ የሰዉ ሕይወት ጥፋት እና የንብረት ዉድመት ጠባሳ ያልሻረባት ኬንያ አሁንም ወደዚያዉ እንዳታመራ ጥንቃቄ እየተደረገ ነዉ። ከናይሮቢ የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ፍቅረማርያም መኮንን ስለዛሬዉ ድባብ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic