ዉጥረት የተሞላ የደህንነት ሁኔታ በማሊ | አፍሪቃ | DW | 06.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ዉጥረት የተሞላ የደህንነት ሁኔታ በማሊ

የኮያማ ቀይ የበረሃ አሻዋ ከምዕራብ አፍርቃ ካሉት በጣም የተዋበ አሻዋ መሆኑን አከባቢዉን የሚያዉቁ ተጓዦች ይመሰክራሉ። ሌሎችም በካኑ አድርጎ በንጄር ዴልታ አቋርጦ በዚህ በተዋባ አሻዋ፣ የጋኦ ተፈጥሮአዊ ቅርፅ የሆነዉን፣ በተለይም ከሰዓት በዋላ ዉብ የሆነዉን የፀሃይ ጥልቀት እየተዝናኑ፣ ጉዞ ማድርግ እንደሚቻል ይጠቁማሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:19
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:19 ደቂቃ

የደንነት ሁኔታ በማሊ

ይህ ግን እስከ 2011 ነበር። ከዚህ ግዜ ጀምሮ የጋኦ ከተማን የሚያቋርጥ የትኛዉንም ጉዞ እና ጉብኝ አቁሞዋል። ምክንያቱም ይላሉ በአፍርቃዉ የፀጥታ ጥናት የሴንጋል ቅርንጫፍ ባልደረባ ኢብራሒም ማኢጋ፣ «እኔ ለሁለት ሳምናታት በጋኦ አካባቢ ነበርኩ። ከከተማዉ 15 ኪሎሜትር ከወጣ በእርግጠኝነት በታጠቁ ሰዎች ልትመታ ትችላለህ። ይህም የሰዎች የመንቀሳቀስ ላይ ችግር አሳድሮዋል።»


የተባበሩት መንግስታ የሕፃናት መርጃ ድርጅት UNICEF በሴሜናዊዉ ማሊ ከ380,000 ባላይ ሕፃናቶች ወደ ትምህርት ቤት መሄድ እንዳልቻሉ ያብራራል። ከ ሴሜናዊዉ ጋኦ 300 ኪ,ሜ ርቆ የሚገኘዉ ኪዳል ተብሎ የሚጠራዉ አከባቢ 80 በመቶ ትምህርት ቤቶች ተዘግቶ እንዳሉም ያስርዳል። እንደ UNICEF ከሆነ በጦርነቱ ግዜ ቤቶች እንደፈረሱ፣ እንደተዘረፉ እናም እንደተያዙ ያትታል። ብዙ አሰተማርዮችም ለደሕንነታቸዉ በመፍራት አካባቢዉን ጥለዉ ተሰደዋል፣ ለተማርዎቹም የየተቀበሩ ፈንጂዎች ስላሉ ወደ ትምርት ቤት መሄድ ትልቅ ስጋት አሰድሮባቸዋል። ይሕንንም ጉዳይ ለማብረድ የጀርመኗ የመከላኪያ ሚኒስቴር ወታደሮችን ወደቦታዉ ለመላክ አቅደዋል።


የጀርመን ወታደሮች የሚዘምቱት እስካሁን እዚያ በሠፈረዉ የፈረንሳይ ጦር ላይ ያለዉን ጫና ለማቃለል ነዉ።
እንደ አዉሮፒያኖቹ አቆጣጠር 2012 የቱሬግ ተዋጊዮችና የእስላማዊ አማፂያን ሰሜናዊ ማሊን ተቆጣጥሮ እንደምገኙ ዘገባዎች ያትታሉ። ሴሜናዊ ማሊ የምትገኘዉ በሳሄል በረሃ ስሆን፣ በስፋቱ ፈረንሳይን የሚያክል እና፣ ከመንግስት ቁጥጥር ዉጭ መሆኑም ይታወቃል። ጋኦ እና ኪዳል አካባቢዎች ከደቡብ አሜርካ የሚመጡ ታላላቅ ቡድኖች አደንዛዥ ዕፅ ወደ አዉሮፓ ለማስተላለፍ ይጠቀሙባታል፣ ለእነሱም ዋነኛ የገቢ ማገኛ እንደሆነ ዘገባዎች ያትታሉ። በቅርብ የማሊ ፓርላማ ምክትል ፕሬዝደንት አማዱ ትኣም መንግሥታቸዉ ብቻዉን ደሕንነትን ማስጠበቅ እንደማይችል እና የዉጭ ሃይል ትብብር እንደሚፈልጉ ለዶቼ ቬሌ ተናግሮዋል።


ከብዙ እስላማዊ ሚሊሻዎች ጋር የድርድር ስምምነት ለማድርግ ቢሞከርም ብዙዎቹ አማፂያን ለመሳተፊ ፊላጎት እንዴሌላቸዉ ተናግረዉ ነበር። በተባበሩት መግስታት የተመሰረተዉ ማሊን የማረጋጋት ተለዕኮ በአጭሩ MINUSMA ተብሎ የምጠራዉ ተልዕኮ ሐላፊ የሆኑት ሞንግ ሃምድ ጉዳዩን አስመልክቶ ስናገሩ፣ «በእርግጠኝነት ብዙ የሽብር ቡድኖች እና የአደንዛዥ ዕፅ አመላላሾች፣ የሰላም ድርድር አካሄዱን ለመግታት እንደሚሞክሩ፣ በደንብ እናዉቀቸዋለን»


ይህ የተባበሩት መግስታት ተለእኮ ብዙም ስኬታማ እንዳልሆነ ዘገባዎች ያሳያሉ። ጀርመን የምትልከዉ ጦር የመንግስታቱን ሃይል እንደምያጠናክርላቸዉ ይጠበቃል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic