ዉጥረት በዓረቡ ዓለም | ዓለም | DW | 18.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ዉጥረት በዓረቡ ዓለም

ከሰሜን አፍሪቃዋ አገር ከቱኒዚያ የተቀጣጠለዉ ህዝባዊ አመፅ ወደዓረቡ ዓለም ከተሻገረ ወዲህ የአካባቢዉ ሀገራት ዉጥረት ይታይባቸዋል።

default

በየመን ቀስ በቀስ እያደገ የሄደዉ ተቃዉሞ ፕሬዝደንቱ ስልጣን ይልቀቁ የሚለዉን ግፊት አጠናክሮ የባህረ ሰላጤዉ አካባቢ ሀገሮችን አደራዳሪነት ሲጋብዝ፤ በሶሪያ አንዴ ሲግል አንዴ ሲቀዘቅዝ የሰነበተዉ የህዝብ ተቃዉሞ ባሳለፍነዉ ሳምንት ማለቂያ መባባሱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። በፀጥታ ኃይሎች ጥይት ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎችን ለመቅበር በተወጣበትም ሆነ ለተቃዉሞ በተሰባሰቡ ዜጎች ፕሬዝደንት ባሺር አልአሳድ መንበራቸዉን እንዲለቁ ሲጠየቅ፤ ህይወታቸዉን ያጡና የተጎዱም መበርከታቸዉ ተነግሯል። በግብፅ የቀድሞ ባለስልጣኖች ወደችሎት ሲመሩ፤ የባህረ ሰላጤዉ ሀገራት ደግሞ ኢራንን ከሰዋል። ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ጂዳ የሚገኘዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ የአካባቢዉን ሁኔታ እንዲያስቃኘን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ነብዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ተዛማጅ ዘገባዎች