ዉይይት፤ ገላጋይ ያጣዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ | ኢትዮጵያ | DW | 27.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዉይይት፤ ገላጋይ ያጣዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃዉሞን ተከትሎ የተደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ የተከሰተዉን የፖለቲካ ቀዉስና አመፅ ለማስወገድ ረድቶ ይሆን? መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የነበረዉን ቀዉስ ለማረጋጋት ረድቷል ሲል ይገልጻል።

 

አንድ ዓመት በደፈነዉ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ብዙ ሕይወት ጠፍቷል። በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ቆስለዋል፤ ታስረዋል፤ ተሰደዋልም። የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዉሞዉ ለማፈን ከወሰዳቸዉ የሐይል እርምጃዎች በተጨማሪ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል። የካቢኔ ሹም ሽር አድርጓልም።ይሁንና ሕዝብ ያነሳቸዉ ጥያቄዎች ተገቢዉን መልስ ባለማግኘታቸዉ መንግሥት በወሰዳቸዉ እርምጃዎች አመጹ ቢቀዘቅዝም ተመልሶ መቀጣጠሉ አይቀርም የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ። ይህ ሁሉ ሲሆን፤ ከፖለቲካ ገለልተኛ የሚባሉት የኃይማኖት መሪዎች፤ የሐገር ሽማግሌዎች እና ምሑራን የት ነበሩ? የሚለዉ ጥያቄ በሰፊዉ እያነጋገረ ነዉ። ዉይይታችን በዚሁ ዙርያ ያተኩራል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic