ዉይይት፤ የ«ኦዴፓ» እና የ« ኦነግ » እርቅ ፋይዳ ተስፋና ስጋቱ | ኢትዮጵያ | DW | 04.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዉይይት፤ የ«ኦዴፓ» እና የ« ኦነግ » እርቅ ፋይዳ ተስፋና ስጋቱ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር «ኦነግ » ወራት ያስቆጠረዉን  ግጭት፣ ዉዝግባቸዉን ለማስወገድ «የመጀመሪያ ደረጃ» የተባለ ስምምነት ባለፈዉ ሰሞን  አምቦ ላይ ተፈራርመዋል። የሁለቱ ወገኖች ተወካዮች ተኩስ ለማቆም መስማማታቸዉ ነዉ የተነገረዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 33:12

የአባ-ገዳዎች በጎ ጎን እንዳለ ሆኖ እርቁ የሕግ ማዕቀፍ ያስፈልገዋል  

በአብዛኛዉ ምዕራብ ኦሮሚያ ዉስጥ ሸምቋል የሚባለዉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሠራዊት አለበት ከተባለዉ «ጫካ» ወጥቶ ማቆያ ሠፈር እንዲሠፍርም ወስነዋል።  ስምምነቱን ከመፈራረማቸዉ በፊት የተቋቋመዉ አስታራቂ ኮሚቴ ከምሁራን፣ ከአባገዳዎች፣ ከኦሮሚያ ገዢ ፓርቲ (ኦዴፓ)ና ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የተወከሉ 71 አባላት ያሉት  መሆኑም ተገልፆአል። ኮሚቴዉ ከሳምንታት በፊት አዲስ አበባ ዉስጥ ሲመሠረት የሁለቱ ጠበኛ ድርጅቶች ወይም የፖለቲካ ማሕበራት ተወካዮች ለመነጋገር-መስማማታቸዉ ለብዙዎች «ብሥራት»፣ ለጥቂቶቹ የትችት፣ ለጥቂቶቹ ደግሞ የጥያቄ ምክንያት ሆንዋል።

 አቶ ሞኔኑስ ሁንዳራ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና በአንቦ ዩንቨርስቲ ጨምሮ በተለያዩ የግል ከፍተኛ ተቋማት የፖለቲካ ሳይንስ መምህር እና ተመራማሪ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ የምስራቅ አፍሪቃ ፖሊስ ጥናት ተቋም ም/ል ዳይሬክተር ፤ ዶ/ር መንግሥቱ አሰፋ በደቡብ ኢትዮጵያ ኮንሶ ዞን የሕክምና ባለሞያ እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተለያዩ ሚዲያዎች አስተያየኃቸዉን በመስጠታቸዉ የሚታወቁ  እንዲሁም ፤ የሰብዓዊ መብትና የፖለቲካ አቀንቃኝ አቶ መስፍን ፈይሳ ሮቢ ሃሳባቸዉን ያካፍሉበት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት «ኦዴፓ» ና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የ« ኦነግ » ወደ እርቅ ለመምጣት የመስማማታቸዉ ፋይዳ ተስፋና ስጋቱን ይመለከታል። 

ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን! 

አዜብ ታደሰ

 

Audios and videos on the topic